አሁን የጥገኝነት ጥያቄ ውሳኔ በፖስታ ይደርሶታል

Nu kan du få asylbeslut i posten – amhariska

እስከ አሁን በነበረው አሰራር፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የጥገኝነትን ውሳኔ የሚያሳውቀው፥ ባለ ጉዳዩን በጽ/ ቤቱ የመሰተንግዶ ክፍል ድረስ ጠርቶ በአካል በማነጋገር ነበር። ያ አሰራር አሁን ተለውጧል። ከማርች (mars) 1 ቀን ጀምሮ በስዊድን የጥገኝነት ጥያቄዎ ውሳኔ መኖሪያ አድራሻው ድረስ በፖስታ ይላክሎታል።

ከማርች (mars)1 ቀን ጀምሮ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የጥገኝነት ጥያቄውን ውሳኔ በተለያየ መንገድ ሊያሳውቆት ይችላል። ውሳኔውን በአንድ የመሥሪያ ቤታችን ጸሐፊ አማካኝነት መስተንግዶ ክፍለ ድረስ ጠርተንዎት እንዲያውቁት ማድረግ ወይም ውሳኔውን በፖስታ በመላክ ሊሆን ይችላል። ውሳኔውን ለባለ ጉዳዩ ማሳወቅ (delgivning) ይባላል፣ ውሳኔውን በፖስታ በመላክ ማሳወቅ ደግሞ ውሳኔ በቀላል መላ ማሳወቅ (förenklad delgivning) ይባላል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔውን በቀላሉ የማሳወቅ መላ በመጠቀም ወሳኔውን ቀደም ብለው በሰጡን የመኖሪያ አድራሻዎ በኩል አንድ ደብዳቤ በፖስታ እንዲደርስዎት ያደርጋል። በሚቀጥለው የሥራ ቀን ደግሞ፣ ውሳኔው እርስዎ ጋር መድረሱን ለማወቅ፣ ሌላ አዲስ የውሳኔ ሰነድ መላካችንን የሚገልጽ መቆጣጠሪያ መልዕክት እንልካለን። በዚህ መቆጣጠሪያ መልዕክት ላይ ውሳኔው የተላለፈበት ዕለት በውል ሰፍሮ ይገኛል። ውሳኔው ወደ እርሶ ከተላከ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔው ደርስዎታል ብሎ ይደመድማል።

በነገራችን ላይ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የኢኮኖሚ ድጋፍንና የመኖሪያ ፈቃድ መራዘምን የሚመለከቱ መረጃዎችን ውሳኔ በቀላሉ ማሳወቅያ መላ (förenklad delgivning) በመጠቀም ቀደም ብሎ ሲያደርስ ቆይቷል።

ስለ ውሳኔውን ያለው መርጃ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔውን በተመለከተ ያለውን መርጃ በቀላሉ የማሳወቅ መላ ማለትም ውሳኔ በፖስታ የመላክ መላን ቢመርጥም ቅሉ፣ እርስዎ የጽሕፈት ቤታችን እንግዳ መስተንግዶ ክፍል (mottagningsenheten) ድረስ እንዲመጡና፥ አንድ ጸሃፊ ጋር እንዲገናኙ የማድረግ አሰራራችን ሁሌ ይኖራል። ከጸሓፊው ጋር በሚገናኙበት ወቅት የውሳኔው ይዘት በአንድ አስተርጓሚ ረዳትነት ይገለጽሎታል። ውሳኔው ከደረስዎ ዕለት በኋላ ሁለት ሳምንታት ከማለፋቸው በፊት፥ ወደ እንግዳ መስተንግዶ ክፍል ከመጡ፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ያንን ዕለት ውሳኔውን ያወቁበት ዕለት አድርጎ ይቆጥረዋል።

ውሳኔ የሚጸናበት ግዜ የሚጀምረው

ውሳኔውን እንዲያውቁ የተደረገበት ዕለት ወሳኝ ነው። ወሳኔውን የማይቀበሉት ከሆነ፣ ውሳኔውን እንዲያውቁ ከተደረገበት ዕለት ጀመሮ ባሉት ሶስት ሳምንታት ግዜ ውስጥ ይግባኝ ማለት ይችላሉ። ውሳኔውን እንዲያውቁ የተደረገበት ዕለት አንስቶ ሶስት ሳምንታት ሲያልፉ ውሳኔ በሕግ የጸና ይሆናል። ከዚያ በኋላ ይግባኝ ማለት አይቻልም።

ይህ ማለት ውሳኔው የሚጸናው፣ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በቀላሉ የማሳወቅ መላ ማለትም ውሳኔ በፖስታ የመላክ መላን (förenklad delgivning) በመጠቀም ወሳኔውን በፖስታ እንዲደርሶት ካደረገበት ዕለት አንስቶ ከአምሥት ሳምንታት በኋላ ነው።

ውሳኔው የጥገኝነት ጥያቄዎን ውድቅ የሚያደርግ ከሆነ፣ ስዊድንን በፈቃድዎ ለቅቀው ለመውጣት በአብዛኛው ሁለት ወይም አራት ሳምንታት ያህል ግዜ ይኖርዎታል፣ ውሳኔው ከጸናበት ቀን አንስቶ ማለት ነው። በዚህ ግዜ ውስጥ ስዊድንን ለቀው ካልወጡ፣ ሲሰጥዎት የነበረውን የመኖሪያ ቤት አገልግሎትና የኢኮኖሚ ድጋፍ ያጣሉ።

በርካታ ውሳኔዎች ሊተላለፉ ይችላሉ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔውን የሚያሳውቅበት መንገድ የተለያየ የሚሆንበት ምክንያት ብለን የምንጠቅሰው፣ አንዳንድ ግዜ እኛ ወዲያው በተግባር ላይ መዋል የማይችል ውሳኔ እንዲያውቁት እናደርጋለን፣ በዚህ ምክንያይ ጥገኝነት ጠያቂው ለውይይት ወደ ጽሕፈት ቤት ድረስ እንዲመጣ ሲጠራ ይጠፋል። ዳሩ ግን ወደ ጽሕፈት ቤታችን ሲጠሩ ባይመጡም ቅሉ፣ ውሳኔው በቀላሉ የማሳወቅ መላ (förenklad delgivning) በመጠቀም፥ ፖስታ ከደረስዎት ዕለት ጀምሮ የጸና ይሆናል።

አድራሻዎን ስለ ማሳወቅ

ትክክለኛ አድራሻዎን የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ማሳወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። አዋቂ የቤተሰብዎ አባላትም ስም በመኖሪያ ቤትዎ በር ላይ ወይም የፖስታ ሳጥናችሁ ላይ በግልጽ ተጽፎ እንዲታይ ማድረግም ያስፈልጋል። የፖስታ ሳጥንዎን በየጊዜው መፈተሽ አይዘንጉ። አድራሻዎን ሲቀይሩ አዲሱን አድራሻ ወዲያውኑ ያሳውቁን።