በስዊድን ኣገር ጥገኝነት ለሚጠይቁ ሁሉ

Till dig som söker asyl i Sverige – amhariska

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትቤት (Migrationsverket) ነው የጥገኝነት ጥያቄህን የሚያየው። በስዊድን ኣገር ጥገኝነት የሚፈቅድ መምሪያ በተባባሩት መንግስታት የስደተኞች ውል፣ በኤውሮጳ ሕብረት የጋራ ህጎችና በስዊደን ኣገር ህግ ሰፍርዋል።

በዚህ የመረጃ ጽሁፍ ዉስጥ አጠር በአለ መንገድ የጥገኝነት ጥያቄህ እንዴት በስደተኞች ጽ/ቤት እንደሚያዝ እንዲሁም ጥገኝነት ጠያቂ እንደመሆንህ መጠን በስዊድን ኣገር ምን ዓይነት መብትና ግዴታውች እንዳለህ ባጭሩ ያብራራል። ወደ ጽሁፍ መጨረሻም ተጨማሪ መረጃ ታገኛለህ። ጥያቄዎች ካሉህ ማቅረብ ትችላለህ።

የጥገኝነት ህጎች

በስዊደን ኣገር ጥገኝነትን የሚመለከቱ ማመልከቻዎች ሁሉ በግለሰብ ደረጃ ናቸው በስደተኞች ጽ/ቤት የሚታዩ። የስዊደን ኣገር ለስደተኞችና በሌላ ምክንያት መጠለያ ለሚፈልጉ፡ የመኖርያ ፈቃድ ይሰጣል።

ስደት

በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ውል መሰረትና በስዊድን ኣገር ህግ፡ ኣንድ ሰው ስደተኛ ወይም ጥገኝነት ፈላጊ ሊባል የሚችለው በሚከተሉትን ምክንያቶችበተረጋገጠ ሁነታ በኣገሪቱ ውስጥ መኖር የሚያስፈራው ሲሆን ነው፤

 • ዘር
 • ብሔር
 • ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ኣቋም
 • ጾታ
 • ጾታዊ ዝንባሌ
 • የኣንድ ልዩ የሕብረተሰብ ክፍል ኣባል በመሆን

ማሳደዱንና ማሰቃየቱ ካገሪቱ ባለስልጣን ሊመጣ ይችላል። ወይም መንግስቱ በሌሎች ቡድኖች ሊደርስ የሚችል ማሳደድናማሰቃየት ሊከላከልልህ የማይችል ሊሆን ይችላል።

በስደተኛነት ተቀባይነት ያገኙ ሰዎች የመኖርያ ፈቃድ የሚሰጣቸው ኣብዛኛውን ግዜ ለሶስት ዓመት ነው።

ኣማራጭ ጥገኝነት ፈላጊ (Alter­na­tivt skydds­be­hö­vande)

በስዊድን ኣገር ህግ መሰረት፡ ኣንድ ሰው ኣማራጭ ጥገኝነት ፈላጊ (Alternativt skyddsbehövande) ተብሎ የሚታወቀው የሚከተሉትን ምክንያቶች ሲኖሩ ነው፤

 • በሞት ልትቀጣ የምትችል ከሆነ
 • ለኣካላዊ ቅጣት፡ ግፍና ስቃይ እንዲሁም ለሌላ ኢሰብኣዊና የሚያዋርድ ቅጣት ልትዳረግ የሚትችል ስትሆን
 • እንደ ሲቪል ግለሰብ በጦርነትና በግጭት ምክንያት ባደጋ ላይ ልትወድቅ ስትችል

የኣማራጭ ጥገኝነት ፈላጊ ደረጃ ፈቃድ ከተሰጠ አብዛናውን ጊዘ የሚሰጣቸው የ 13 ወራት የመኖርያ ፈቃድ ነው ።

የጥገኝነት ማመልከቻህን በሚመለከት

በስዊድን ኣገር ጥገኝነት ለመጠየቅ ከፈልግክ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት (migrationsverket) በግልህ መሄድ ይገባሃል። የስደተኝነት መጠየቂያ ክፍል(ansökningsenheten) የጥገኝነት ማመልከቻህም ተቀብሎ ይመዘግበዋል።

ከዚያ በኋላ፡ ፎቶግራፍ ትነሳለህ። የጣት ኣሻራ ትሰጣለህ። የጣት ኣሻራ የሚያስፈልግበት ዋና ምክንያቶች አንዱ በሌላ የኤውሮጳ ሕብረት ኣገሮች ጥገኝነት የጠየቅክ ኣለመሆንህን ለማረጋገጥ ነው።

የጉዳይህን የያዘ አንድ ሰው (handläggare) ትገናኛለህ። እርሱ ከኣንድ ኣስተርጓሚ ጋር በመሆን ስለ ማንነትህ፡ ለምን ኣገርህን ትተህ እንደመጣህና እንዴት ወደ ስዊድን ኣገር እንደ ገባህ ለማወቅ ጥያቄ ሊያቀርብልሃል። እንዲሁም ቤተሰቦችህንና ጤንነትህን በሚመለከት ትጠየቃለህ። ይህን ማድረጋችን፡ ማመልከቻህን ለምርመራ ለማዘጋጀት ነው። በጥገኝነት ማመልከቻህ በኩል በሚደረገው የምርመራ ግዜ፡ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ የመስጠት ጊደታ ይኖርብሃል።

ልዩ ጥያቄ ሲኖርህ፡ ለምሳሌ የሆነ ስንኩልነት፡ ኣካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ወይም የኣእምሮ ችግር ሲኖርህ፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትን ኣሳውቅ። ጥገኝነት በምትጠይቅበት ግዜ፡ ስንኩልነትህ ከስደተኞች ጽ/ቤት ኣባሎች ሃሳብህን ለማስተላለፍ የሚያስቸግርህ ሲሆን፡ እርዳታ መጠየቅ ትችላለህ።

የስደተኝነት መጠየቂያ ክፍል፡ የጥገኝነት ጥያቄ በሚመለከት ስራው እንዴት እንደሚካሄድ ለማወቅ መረጃ ሊሰጥህ ይችላል። ጥያቄዎች ለማቅረብም ትችላለህ። የጥገኝነት ማመልከቻህ ከተመዘገበ በኋላ፡ የጥገኝነት ጥያቄህን በሚመለከት ግዜያዊ ደረሰኝ kvitto) ይሰጠሃል። ደረሰኙን፡ ኤል.ኤምኤ LMA-kort ካርድ እስኪሰጥህ ድረስ ካንተ ጋር ይሁን። ካርዱ፡ ኣንተ ራስህ ጥገኝነት ፈላጊ መሆንህን ያሳያል።

ማን መሆንህን ኣሳውቅ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትቤት የጥገኝነት መብት ያለህ ወይም የሌለህ መሆኑን ለመገምገም እንዲችል፤ ማን መሆንህና ከየት እንደመጣህ ማስረዳት ኣለብህ። ይህንን ለማረጋገጥ የሚያገልግል የበለጠ መንገድ፡ ፓስፖርት ወይም የመታወቅያ ወረቀት ማቅረብ ነው። የመታወቅያ ሰነዶች በኣገርህ ባሉት ባለስልጣኖች የተሰጠ መሆን ኣለበት። እንዲሁም ፎቶህ እዛው መኖር ኣለበት። ሰነዱ፡ ስምህንና ዜግነትህ እንዲሁም የተወለድክበት ቀን የያዘ መሆን ይገባል።

ማንነትህን የሚገልጹ ሰነዶች ማቅረብ ያንተው ሃላፊነት ነው። ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ስትመጣ ካልያዝካቸው ማመልከቻህን የተሟላ እንዲሆን በማለት የጉዳዩ ኣስኪያጅ/ኣመቻች (handläggare) ሰነዶቹን ቶሎ ብለህ እንድታቀርባቸው ይጠይቃል።

ማንነትህን የሚያረጋግጡ ሰነዶች ለማምጣት የሚያስቸግርህ ከሆነ፡ ለማምጣት እየሞከርክ መሆንህ ለስደተኞች ጽ/ቤት ኣሳውቅ።ሌላ ማንነትህን የሚያረጋግጥ ሰነድ ካለህ፡ ለምሳሌ የመኪና መንጃ ፈቃድ፡ የልደት ምስክር፡ የዜግነት ምስክር ወይም የውትድርና ካርድ... ልታቀርባቸው ትችላለህ። እንዲህ የመሳሰሉ ሰነዶች ግን ብቻቸውን ማንነትህን ለማረጋገጥ በቂ ኣይደሉም፡ ሆኖም ህሉም ባንድ ላይ ሁነው፡ በዚያ ላይም ኣንተ በምትሰጠው የህይወት ታሪክና ስለ ኣገርህ ሁኔታ ተጨምሮ ማንነትህን የሚታመን ሊያደርጉት ይችላሉ።

ማን መሆንህ ለመግለጽ የተባበርክ እንደሆነ፡ ለውሳኔው እየተጠባበቅክ እያለህ ኣብዛኛው ግዜ ስራ የመስራት መብት ሊሰጥህ ይችላል።

የትኛው ኣገር ጉዳይህን ማየት እንዳለበት ራስህ መምረጥ ኣትችልም  (የዱብሊን መምሪያዎች)

የጥገኝነት ማመልከቻህ ካቀረብክ በኋላ፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትቤት ጉዳይህን በስዊድን ኣገር ወይም በሌላ የኤውሮጳዊ ሕብረት ኣገሮች የሚታይ መሆኑን ለመወሰን ምርመራ ያካሂዳል። ወደ ስዊደን ከመምጣትህ በፊት በሌላ የኤውሮጳዊ ሕበረት ኣገር ቪዛ ኣግኝተህ ከሆነ፡ ወይም ሌላ የመኖርያ ፍቃድ ያገኘህ ከሆነ ወይም ጥገኝነት ጠይቀህ ከሆነ፡ ወደ ኣገሪቱ እንድትመለስ ሊያደርግህ ይችላል። ህጉ በዱብሊን መምርያ ሰፍሮ ይገኛል። ስለ ጉዳዩ በተጨማሪ የሚከተለውን የጽሁፍ መረጃ ኣንብብ፤ ''በኤውሮጳ ሕብረት ኣገሮች ጥገኝነት ጠይቄ ነበር – የትኛው ኣገር ነው ጉዳዬን የምትመረመረው?'' (ብሮሹሩ በሁሉ ቋንቋ ማግኘት ኣይቻልም)

በመጠባበቅ ላይ እያለህ

የጥገኝነት ማመልከቻህ በስዊድን ኣገር ውስጥ የሚታይ ከሆነ፡ ውሳኔ እስኪሰጥህ ድረስ እዚሁ ሁነህ መጠበቅ ትችላለህ። በዚያን ግዜ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የሰራተኞች ክፍል ከሆኑት የመቀበያ ክፍሎች (mottagningsenheter) ካንዱ ጋር መገኛነት ያስፈልገሃል። ነገር ግን የክፍሉ ኣባሎች ጥገኝነት የምታገኝ መሆንህ ወይም ኣለመሆንህ ሊወስኑ ኣይችሉም። ክፍሉ ገንዘብና መኖርያ-ቤት በሚመለከት ጉዳይ ብቻ ነው የሚረዳህ። ለማመልከቻህ ዉሳኔ ሲላክ ካንተ ጋር ግንኙነት የሚያደርግም ራሱ የመቀበያ ክፍሉ ነው። እርሱ ስለ ውሳኔው መረጃ ይሰጥሃል፡ ምን ማድረግ እንዳለብህም ይነግርሃል።

ኣስፈላጊ መረጃ

የስደተኞች መቀበያ ክፍል (mottagningsenheten) ለጋራ ለስብሰባ ሊጠራህ ይችላል። በስብሰባው ላይ ጥግጠኝነት ፈላጊው ማወቅ የሚገባው ሁሉ ይነገርሃል። ለምሳሌ፡ ስለ የምትኖርበት ቤት፡ ገንዘብ፡ በሽታና እንክብካቤ ሊሆን ይችላል። ህጎችን በሚመለከት፡ እንዲሁም ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎችን የሚረዱ ሌሎች ድርጅቶችን በሚመለከት መረጃ ይሰጥሃል። ይህ፡ ውሳኔው ለማወቅ በምትጠባበቅበት ጊዜ ልትጠቀምበት የምትችል በጣም ኣስፈላጊ መረጃ ነው።

በመጠየቅያ ክፍሉና በመቀበያ ክፍሉ በኩል ብዙ መረጃ ይሰጥሃል። ኣንዳንድ ግዜ መረጃው በአንደ ሲሰጥ የበዛ ሊመሲል ይችላል። ነገር ግን በሌላ ኣጋጣሚ የስራ ኣስኪያጁን ስታገኘው ጥያቄህን ለማቅረብ እንድትችል ዘንድ፡ የምትቀበላቸውን ወረቀቶች ኣንብባቸው፡ ካንተ ጋርም ያዛቸው።

በስደተኞች ጽ/ቤት በሚስተዳደር መኖርያ-ቤት የምትኖር ከሆነ፡ ኣንዳንድ ግዜ በስራ ወይ ለጉብኝት የሚመጡት የጽ/ቤቱ ኣባላሎች ልታገኛቸው ትችላለህ። እነርሱ ስለ አንተ የጥገኝነት ጉዳይ በሚመለከት መልስ መስጠት ኣይችሉም፡ ነገር ግን ኣንዳንድ ኣስፈላጊ መረጃ ስትፈልግ ሊሰጡህ ይችላሉ።

የጥገኝነት ጉዳይ የሚመለከት ምርመራን መጠባበቅ

የጥገኝነት ማመልከቻህ ለመመርመር ረጂም ግዜ ይወስዳል። ሆኖም የግዜው ርዝመት እንደ ኣመልካቹ ይለያያል።

በምርመራው ግዜ፡ በምን ምክንያት በስዊድን ኣገር ጥገኝነት መጠየቅ እንደፈለግክና ምን ችግር ኣጋጥሞህ እንደነበር፡ እንዲሁም ወደ ኣገርህ ስትመለስ ምን ችግር እንደሚያጋጥምህ በተጨማሪ ማብራራት ይኖርብሃል።

ውሳኔ ከማግኘትህ በፊት፡ለብዙ ቀጠሮዎች ልትጠራ ትችላለህ። በቀጠሮ ላይ መገኘት ይኖርብሃል። እንደገና ቀጠሮ መያዝ የውሳኔው ግዜ ሊያራዝምብህ ስለሚችል፡ ልክ በቀጠሮህ ላይ መገኘት ይመረጣል።

የኣድራሻ መረጃ ላክ

ውሳኔው በምትጠባበቅበት ግዜ ወደ ሌላ ቦታ የተዛወርክ ከሆነ፡ ለምርመራና ለስብሰባ ልናገኝህ እንድንችል፡ ኣዲሱን ኣድራሻህ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣሳውቅ። ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የሚመጣውን መረጃ እንዳያመልጥህ፡ የሚመጣውን መልእክቶች ሁሌ ማየትና ማንበብ እንዳለብህ ኣትርሳ።

ኤል.ኤም.ኦ ካርድ LMA-kort

በስዊድን ኣገር ጥገኝነት በምትጠይቅበት ግዜ የመጠየቅያ ደረሰኝ (kvitto) ካርድ ይሰጠሃል። ከስደተኞች ጽ/ቤት ጋር ስትገናኝ የምትጠቅሰው ቍጥር በደረሰኙ ላይ ተጽፏል። ከዚህ በመነሳት የጉዳይህን የሚያይ ሰው ፋይልህን በቀላሉ ሊያገኘው ይችላል። አመ ካርዱን ልታመጣ ትችላለህ። ካርዱ ኤል.ኤምአ ካርድ LMA-kort ይባላል። እርሱ ጊዘአዊውን ደረሰኝ የሚተካ ነው።

ጥገኝነት ጠያቂ መሆንህና ውሳኔ እስኪሰጥህ ድረስ ደግሞ በስዊድን ኣገር ለመቆየት መብት እንዳለህ ለማረጋገጥ፡ ኤል.ኤም.ኦ ካርዱ LMA-kort ሁሌ ካንተ ጋር መያዝ ይኖርብሃል። ወደ ህክምና ስትሄድ ኤል.ኤም.ኦ ካርዱ LMA-kort ካንተ ጋር ውሰደው፡ ምክንያቱም ያው መብትህ የሆነውን ህክምና በቅናሽ ዋጋ ልታገኝ ትችላለህ።

መኖርያ ቤት

መኖርያ ቤት በሚመለከት፡ ራስህ ለመያዝ ወይም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ባዘጋጀልህ ቤት ለመኖር ትችላለህ። የግል ገንዘብ ካለህ፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ለሚሰጥህ ቤት ኪራይ ትከፍላለህ። በራስህ ጥረት ቤት ካገኘህ ደግሞ ኪራዩ ራስህ ነው የምትከፍለው።

በስደተኞች ጉዳይ ጽ. ቤት (Migrationsverket) የመኖሪያ ሥፍራ ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ የመኖሪያ አካባቢውን መምረጥ አይችሉም፣ ኣንዲሁም በጥበቃ ግዜ ላይ እያሉ ሥፍራ ለቀው ሊሄዱ የሚችሉበት ሁኔታ ይኖራል ማለት ነው። የመኖሪያ ቤትዎን ጉዳይ በግልዎ አመቻችተው ወደ አዲሱ ቤት የሚቀይሩ ከሆነ አድራሻዎን ለስደተኞች ጉዳይ ጽ. ቤት ማሳወቅ እንዳለብዎት አይዘንጉ። በስደተኞች ጉዳይ ጽ. ቤት የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት አለባቸው የሚባሉ አካባቢዎች ሥም ዝርዝር አለው። በእነዚህ አካባቢዎች መኖር የመረጠ ሰው ከስደተኞች ጉዳይ ጽ.ቤት ሊያገኝ የሚችለውን የኢኮኖሚ ድጋፍ የማግኘት መብቱን ሊያጣ ይችላል። አድራሻዎ በነዚህ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ማጣራት ከፈለጉ ይህን ድረ-ገጽ migrationsverket.se/asyl ይጎብኙ።

የተለየ ችግር ካለብህ፡ ልዩ ቤት ለማግኘት መብት ኣለህ። ለምሳሌ፡ ኣንድ የሆነ ስንኩልነት፡ ኣካላዊ ወይም ስነ-ልቦናዊ ችግር ካለህ፡ ወይም ልዩ የጾታ ዝንባሌ ሲኖርህ፡ ወይም እንደ ሴት መጠን እርጉዝ ስትሆኚ፡ ወይም በዕድሜ የገፋ ሰው ስትሆን። ችግርህ ቶሎ ለስደተኞች ጽ/ቤት ንገራቸው፡ እኛም የሚስማማህና ደህንነትህን የሚጠብቅልህ ቤት ልናገኝልህ የሚቻለውን እንሞክራለን።

በመኖርያ ቤት የሚኖር ሰው ሁሉ የርስበርስ መከባባር ማሳየት ይኖርበታል፡ ይህም ሃይማኖት፡ ባህል ወይም ጾታዊ ዝንባሌ ሳይለይ መከናወን ኣለበት። በዛው በምትኖርበት ቤት ውስጥ ደህንነት ካልተሰማህ ለስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣሳውቅ/ኣመልክት።

ጤናና ህክምና

ኣንተ እንደ ጥገኝነት ጠያቂ ለኣስቸኳይ ህክምናና ለኣስቸኳይ የጥርስ ህክምና እንዲሁም ሊቆይ ለማይችል ህክምና መብት ኣለህ። ምን ዓይነት ህክምና እንደሚያስፈልግህ የሚወስን ክሊኒኩ ብቻ ነው። ኤል.ኤም.ኦ ካርዱ LMA-kort ስታሳይ በህክምና ግዜና መድሃኒት ስትገዛ የዋጋ ቅናሽ ታገኛለህ። ጥገኝነት የሚጠይቁ ህጻናትና ዕድሜኣቸው ከ 18-ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች፡ ልክ እንደ ሌሎች
በስዊደን ኣገር የሚኖሩ ህጻናትና ወጣቶች የነጻ ህክምና መብት ኣላቸው።

ጥገኝነት የሚጠይቁ ሁሉ የማይከፈልበት ኣጠቃላይ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ወደ ጤና ጣብያ ይጠራል። ኣጠቃላይ የጤና ምርመራ የጥገኝነት ጥያቄህን ኣይነካውም። ምናልባት ኣንድ ዓይነት በሽታ ካለህ ቶሎ ብለህ እንድትታከም በማሰብ ብቻ ነው። በምርመራው ላይ ጤንነትህ በሚመለከት ምክር ሊሰጥህ ነው፡ የደም ምርመራም ልታደርግ ነው። እንዲሁም በስዊድን ኣገር ጤናና ህክምና በሚመለከት መረጃ ሊሰጥህ ነው። ልዩ ህክምና እንዲደረግልህ ዘንድ፡ የስንኩልነት ችግር፡ በሽታ ወይም ሌላ ችግር ካለህ ለጤና ጣብያው ሰራተኛ ኣነጋግር።

የጤና ጣብያው ሰራተኛ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣባል ኣይደለም፡ ምስጢርም ኣያወጣም።

ስራ

እንደ ጥገኝነት ጠያቂ፡ በስዊደን ኣገር ያለ ስራ ፈቃድ መስራት ትችላለህ። ሆኖም፡ የሚከተለውን ማሟላት ይኖርብሃል፤ ከ

 • ጉዳይህ በስዊደን ኣገር የሚታይ ሲሆን
 • ማንነትህን ለማረጋገጥ ስትተባበር
 • የጥገኝነት ጥያቄህ መሰረተ ቢስ ካልሆነ ወይም ካልታመነ

የተጠቀሱትን ነጥቦች ካሟላህ ለመስራት መብት ኣለህ።

በስራ ላይ እያለህ የጥገኝነት ጥያቄህ ውድቅ ሲሆን ኣገሪቱን ትተህ እስክትሄድ ድረስ ወይም ለመሄድ እስከተባበርክ ድረስ ስራህን መቀጠል ትችላለህ። መኖርያ ፈቃድ ካገኘህ ግን ስራህ ቀጣይ ነው።

ክፍት የስራ ቦታ ለማግኘት ስትፈልግ ከሰው ኃይል ቢሮ (Arbetsförmedlingen) ጋር በዚህ የኢንተርነት ኣድራሻ ተገናኝ፤ (www.arbetsformedlingen.se External link, opens in new window.)

የገንዘብ እርዳታ

እርስዎ ሥራ በመሥራት የሚተዳደሩበት እድል ከሌለዎት ወይም በግልዎ የሚያገኙት ምንም ዓይነት ገንዘብ ከሌለዎት ከስደተኞች ጉዳይ ጽ. ቤት ዕለታዊ ድጎማ (dagersättning) ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ. ቤት የሚሰጠው የድጎማ ገንዘብ የምግብ፣ የአልባሳትና ለሌሎች ግለሰባዊ ወጪዎችን መሸፈን የሚችል ነው። ከስደተኞች ጉዳይ ጽ. ቤት ድጎማ ማግኘት ከጀመሩ በኋላ የኢኮኖሚ ሁኔታዎ ከተቀየረ ማለትም ደሞዝ የሚያገኙበት ሥራ ከጀመሩ ወይም መኖሪያ ቤት አድራሻ ቢቀይሩ፣ ይህንኑ መሳወቅ ይኖርብዎታል። የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮት አለባቸው የሚባሉ አካባቢዎች ዘንዳ መኖሪያ ቤት ቢቀይሩ ዕለታዊ ድጎማ የማግኘት መብትዎን ሊያጡ ይችላሉ። አድራሻዎ በእነዚህ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ማጣራት ከፈለጉ ይህን ድረ-ገጽ migrationsverket.se/asyl ይጎብኙ።

በተመሳሳይ መንገድ፣ በእውነት ከሚኖሩበት አድራሻ የተለየ ሌላ አድራሻ ቢሰጡ፣ ለምሳሌ የፖስታ ሳጥን ቁጥር አድራሻ ቢሰጡ፣ ዕለታዊ ድጎማና ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ የማግኘት መብትዎን ሊያጡ ይችላሉ። ልክ ያልሆነ መረጃ መስጠት ወይም መሰጠት የነበረበትን መርጃ ማስቀረት ወንጀል ነው፣ ስለሆነም የስደተኞች ጉዳይ ጽ. ቤት ጉዳዩን ወደ ፖሊስ የማመልከት እርምጃ ሊወስድ ሁሉ ይችላል።

ትምህርት-ቤት

ጥገኝነት የሚጠይቁ ህጻናት ወይም ወጣቶች በሙሉ ወደ ኣጸደ-ህጻናት (ኪንደርጋርተን) ሆነ ትምህርት-ቤት ለመሄድ መብት ኣላቸው።ጥገኝነት የሚጠይቁ ህጻናት ወይም ወጣቶች በሙሉ ልክ እንደ ሌሎቹ በኮሙን ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ለኪንደርጋርተን ትምህርት መብት ለመኖር ሓላፊነቱ የሚሸከመው የምትቀመጥበት ኮሙን ነው። ኮሙኑ ለልጅህ በትምህርት-ቤት በቀላሉ ቦታ እንዲያገኝለት ዘንድ፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የልጅህ ስም፡ የልደት ቀን፡ ቋንቋ፡ ኣገርና የጉዳዩ ቍጥር በሚመለከት መረጃ ወደ ኮሙኑ እንዲልክ መፍቀድ ይገባሃል። ወደ ኮሙኑ ራስህም ሂደህ ልታነጋግራቸው ትችላለህ፡ ልጆችህ ወደ ኪንደርጋርተን ወይም ወደ መደበኛ ትምህርት-ቤት ለመሄድ እንደሚፈልጉም ንገራቸው።

ጎልማሳ ሁነህ በስዊድን ኣገር መኖርያ ፈቃድ ስታገኝ፡ ኤስ.ኤፍ.ኢ (sfi) በሚባለው ለወጣተኞች የሚመለከት ትምህርት-ቤት መማር ትችላለህ። ይሁንና፡ የውሳኔ መልስ እየተጠባበቅክ እያለህ የስዊድን ቋንቋ መማር ብትፈልግ፡ የስዊድን ቋንቋ ትምህርት የሚሰጡ ኣያሌ የበጎ ፈቃድ/መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የትምህርት ፈደረሽኖች ኣሉ። በኣከባቢህ የስዊድን ቋንቋ ስልጠና የሚሰጡ ተቋሞች መኖራቸው ለማወቅ ለመቀበያ ክፍል (mottagningsenhet) ጠይቅ።

የበጎ ፈቃድ/መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (Frivil­lig­or­ga­ni­sa­tioner)

በኣብዛኛው ኣከባቢ የበጎ ፈቃድ/መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለጥገኝነት ፈላጊዎች የሚያገልግል  የትምህርት ፈደረሽንና ቤተክርስትያናዊ ፕሮግራሞች ያዘጋጃሉ። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በኣከባቢህ ውስጥ ምን ዓይነት ድርጅቶች እንዳሉ ሊያሳውቅህ ይችላል። ድርጅቶቹ በሙሉ በትናንሽ ኣከባቢዎች ኣይገኙም። ከኣንድ ልዩ ፕሮግራም ያለው ድርጅት ጋር ለመገናኘት ከፈለግክ ለመቀበያ ክፍል (mottagningsenhet) ጠይቅ።

ጥገኝነትን የሚመለከት ምርመራ

የጥገኝነት ጥያቄን በሚመለከት የሚደረገው ምርመራ፡ በኣስተርጓሚ በኩል የጥገኝነት ጥያቄህ ምክንያት በተጨማሪ ልታብራራው ትችላለህ፣፡ ለምን በስዊድን ኣገር ጥገኝነት እንደ ፈለግክ ይመለከታል። ኣገርህን ትተህ የመጣህ ራስህ ስለሆንክ፡ ኣንተ ነህ ምክንያቱ የምታውቀው፡ ስለዚህ በኣገርህ ውስጥ ሳለህ ምን እንዳጋጠመህና ተመልሰህ ለመሄድ ብትገደድ ደግሞ ምን እንደሚያጋጥምህ ማብራራት በጣም ኣስፈላጊ ነው። ላንተ በተለይ ምን እንዳጋጠመህ እንጂ፡ ባገርህ ውስጥ ያለው ሁኔታ መተንተን ኣያስፈልግም።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ስለ ሰጠሀው ምክንያት በቂ ግምገማ ለማድረግ የሚችለው፡ ያው ውሳኔ ለመስጠት ኣስፈላጊ የሆነው ካገርህ እንድትወጣ የገፋፋህ ምክንያት ስታብራራው ብቻ ነው። የጉዳይህን የያዘ ኣንተን ለመርዳት ሲል በማመልከቻህ ውስጥ ስለሚገኝ ኣስፈላጊ ነጥብ ላይ ጥያቄ ሊያቀርብልሃል።

የሰጠሀው መረጃ የሚያጠናክር ሌላ ነጥብ ካለህ በምርመራ ግዜ ይዘሀው ና። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ሰነዶቹን ሊያስተረጉማቸው ይችላል።

ልትገልጻቸው የሚያስቸግሩ ነገሮች

ኣንዳንድ ነገሮች ልትወያይባቸው የሚያዳግቱ ናቸው፡ በዚያ ላይ የበለጠ ጠቃሚ ሊሆኑም ይችላሉ። የጉዳዩን የሚመለከተው ሰው (handläggare) ምስጢር የመጠብቅ ህጋውዊ ግዴታ ኣለበት። ያልከውን ነገር ደግሞ ጉዳይህን ከሚመረምሩ ሰዎች ጋር ካልሆነ በስተቀር ከሌሎች ሰዎች ጋር ኣይነጋገርበትም። ኣስተርጋሚው ቢሆንም ልክ እንደ የጉዳዩ ኣስኪያጅ/ኣመቻች ምስጢርን የመጠበቅ ግዴታ ኣለበት። ከፈለግክ፡ ምርመራው ለጊዜው እንዲቆም ጥያቄ ማቅረብ ትችላለህ።

በተለይ ሴት ወይ ወንድ የጉዳይ መርማሪ ብትፈልግ ከምርመራው በፊት ኣሳውቅ።

የህግ ረዳት

ኣብዛኞቹ የጥገኝነት ጠያቂዎች የህግ ኣማካሪ (offentligt biträde) ለማግኘት መብት ኣላቸው። ጠበቃ ለማግኘት መብት ካለህ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ጉዳይህን የሚከታተል ልምድ ያለው የህግ ሰው ሊመድብልህ ይችላል። እርሱም ጉዳይህ በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በሚመረመርበት ግዜ የህግ እገዛ ይሰጥሃል።

ኣማካሪውን የሚመድበውና የሚከፍለው የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤቱ ነው፡፣ ሆኖም ኣማካሪው ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤትና ከሌሎች መንግስታዊ ተቋሞች ተጽዕኖ ነጻ ነው። የራስህን ኣማካሪ የሚሆንህን ሰው ማቅረብ ትችላለህ፡ ሴት ወይም ወንድ መሆናቸውም መምረጥ ትችላለህ። ነገር ግን ይህን በሚመለከት ከምርመራው በፊት ማሳወቅ ይኖርብሃል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤቱ የሚከፍለው ኣማካሪ እንዲኖርህ መብት ከሌለህም ራስህ የምትከፍለው ኣማካሪ ልትቀጥር ትችላለህ።

የኣስተርጓሚ ስራና ሚና

በኣብዛኛው ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የሚደረግ ግንኙነት፡ ኣስተርጓሚው የተባለውን ሁሉ ነው የሚተረጕመው። ኣብዛኛው ግዜ ኣስተርጓሚው በክፍሉ ውስጥ ኣለ፡ ወይም ደግሞ በተለፎን ወይም በተንቀሳቃሽ ፊልም ይሳተፋል። ኣስተርጓሚው ያ የምትለውን ነገር ሁሉ በደምብ እንዲተረጉምልህ፡ ስትናገር ሳለህ ኣስተርጓሚው ግዜ እንዲያገኝ በማለት ለኣፍታ ኣቁም።

ኣስተርጓሚዎች የሚከተሉት መመሪያ ኣላቸው። ኣስተርጓሚ ከመጀመሩ በፊት፡ ለባለ ጉዳዮቹ ስራውን፡ ምስጢር መጠበቁን እንዲሁም የተባለውን ሁሉ ለመተርጎም ያለበት ግዴታን በሚመለከት በደምብ ይገልጽላቸዋል። ኣስተርጓሚው የተባለውን እንጂ ጨምሮ ወይም ቀንሶ ኣይተረጉምም። ወገንተኛ ኣይሆንም ወይም ኣያዳላም፡ ማለት፡ ፖለቲካን ሃይማኖትን በሚመለከት ወይም በሌላ ጉዳይ ላይ ያለው ኣቋም ወይም ኣስተያየት መግለጽ ኣይችልም። ላንድ ወገን መደገፍ ኣይችልም፡ ማለት በመሃል ጣልቃ በመግባት ኣንዱን ወገን ማገዝ ወይም ከሌላ ወገን ያለውን ኣስተያየት ወይም ድጋፍ መግለጽ ኣይገባውም።

ኣስተርጓሚው የሚለውን መረዳት ቢያቅትህ ወይም በሆነ ምክንያት ቅሬታ ቢሰማህ፡ ሓሳብህን መግለጽ ይኖርብሃል። በዚህ ላይ ንግግሩም እንዲቋረጥ በማድረግ ሌላ ኣስተርጓሚ እንዲያመጡልህ መጠየቅ ትችላለህ። ሴት ወይም ወንድ ኣስተርጓሚ ብትፈልግ ደግሞ ኣስቀድመህ ኣሳውቅ።

ውሳኔ

የመኖርያ ፈቃድ የተሰጠህ ከሆነ

የመኖርያ ፈቃድ ከተሰጠህ በስዊድን ኣገር መኖርና መስራት ትችላለህ። የመኖርያ ፈቃድ ከወሰድክ በኋላ ወደ ቀረጥ ሰብሳቢ ባለስልጣን (Skatteverket) በመሄድ ተመዝገብ። የብሄራዊ መታወቅያ ወረቀት ቍጥር (personnummer.) ይሰጡሃል። የመኖርያ ፈቃድ እንደ ተሰጠህ የሚያረጋግጥ ከስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የመኖርያ ፈቃድ ካርድ ይሰጥሃል። ካርዱ ወደ መቀበያ ክፍል ነው የሚላከው።

በስዊድን ኣገር የሚሰጥ ኣብዛኛው የመኖርያ ፈቃድ በግዜ የተገደበ ነው። ለኣንድ ዓመት ወይም ለሶስት ዓመታት ያገለግላል።

የፈቃድ ማራዘም

በግዜ የተገደበውን የመኖርያ ፈቃድህ ሲያበቃ፡ ለማራዘም ማመልከት ትችላለህ። ይሁንና፡ ማመልከቻው የምታቀርበው የመኖርያ ፈቃድህ ከመውደቁ በፊት ነው። ሆኖም፡ የምታቀርበው የማራዘሚያ ጥያቄ ከሶስት ወር በፊት ኣስቀድመህ ኣትላከው።

ገና ከለላ ወይም መጠጊያ ብትፈልግ፡ የመኖርያ ፈቃድህን ልታራዝመው ትችላለህ።

ጉዳይህ ወይም ማመልከቻህ ውድቅ ሲሆን

ማመልከቻህ ውድቅ የሚሆንበት ምክንያት፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣንተ በስዊደን ኣገር ለመኖር በቂ ምክንያት የለህም በሚል ግምገማ ላይ በመድረሱ ነው። ጉዳይህ ውድቅ ሲሆን፡ ሁለት ኣማራጭ ብቻ ነው ያለህ፤ ውሳኔውን መቀበል ወይም ደግሞ ይግባኝ ማለት።

ጉዳይህ ውድቅ ሲሆን የማባረር ወይም የማስወጣት ውሳኔ ይሰጥሃል። የማባረሩ ጉዳይ ውሳኔው በተግባር ላይ ከዋለበት ጀምሮ በተለምዶ ኣራት ዓመት ይወስዳል። በነዚህ ኣራት ዓመቶች ውስጥ እንደገና ወደ ስዊድን ኣገር ብትመጣ እንደገና ትባረራለህ። በዚያን ግዜ ጉዳይህ እንዲታይልህ መብት የለህም፡ ከስደተኞች ጽ/ቤትም እርዳታ ኣታገኝም።

የመኖርያ-ቤት መብትና የገንዘብ እርዳታ ማቋረጥ

የጥገኝነት ጥያቄህ ውድቅ ሲሆን፡ የኤኮኖሚ እገዛ በሚመለከት መብት የለህም። ይህ፡ ጎልማሶች ሁነው ከኣንድ ዕድሜው ከ 18 ዓመት በታች ሆኖ በሞግዚትነት ከሚያሳድጉት ልጅ የማይቀመጡ ሰዎችም ይመለከታል። ኤኮኖምያዊ እገዛ ሲባል ለምሳሌ ዕለታዊ ኣበልና በስደተኞች ጽ/ቤት ስር የሚተዳደር ቤት ውስጥ መኖርን ያጠቃልላል። መብቱ የሚቆመው፡ የማባረሩ ውሳኔ በተግባር ላይ መዋል ሲጀምርና ይግባኝ ማለት በማይፈቀድበት ግዜ ነው፡ ወይም ያው በፍላጎትህ ወደ ኣገር ቤት የምትመለስበት ግዜ ሲተላለፍ ነው። ስለዚህ ከስዊድን ኣገር መውጣት ኣለብህ።

ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች በስዊድን የስደት ኤጄንሲ (Migration Agency) ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት ውስጥ ሊቆዩ እና ስዊድንን ለቀው እስከሚወጡ ወይም በሌላ ምክንያት ከስደተኞች መቀበያ ማዕከል እስኪወጡ ድረስ የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብታቸውን ሊያጠብቁ ይችላሉ።

ይግባኝ ለማለት ስትፈልግ

ይግባኝ ለማለት ስትመርጥ፡ ፍርድ-ቤቱ ውሳኔውን እንደገና እንዲያየው ስለ ፈለግክ ነው። ስለዚህ፡ የይግባኝ ማመልከቻህ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ነው የምትልከው። ሆኖም፡ የይግባኝ ጽሁፉ ውሳኔው በተግባር ላይ ከመዋሉ በፊት ወደ ፍርድ-ቤት መድረስ ይገባል። ይህም፡ ውሳኔው ከተቀበልክበት ቀን ጀምሮ ለሶስት ሳምንት ይሄዳል። ኣማርካሪ ካለህ፡ ሊረዳህ ይችላል።

በመጀመርያ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት የይግባኝ ጽሁፍህ የሚለወጥ ነገር ካለው ለማየት ያነበዋል። ይሁን እንጂ፡ የሚቀየር ነገር የሌለው መሆኑ ከተረዳ በኋላ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ፍርድ-ቤት ይልከዋል። ፍርድ-ቤቱን ጉዳዩ ያየዋል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ፍርድ-ቤት ከሚሰጠው ውሳኔ ካልተስማማህ፡ ጥያቄህን ወደ የስደተኞች ከፍተኛ ፍርድ-ቤት ልትልከው ትችላለህ።

ነገር ግን የስደተኞች ከፍተኛ ፍርድ-ቤት ለመጪው ውሳኔዎች መምርያ ሊሆኑ ለሚችሉት ልዩ ጉዳዮች ብቻ ነው የሚያይ። ሆኖም የስደተኞች ከፍተኛ ፍርድ-ቤት ኣቤቱታህን ለማየት ካልፈለገ ኣስቀድሞ የተሰጠህን ውሳኔ በተግባር ላይ ይውላል።

ሃሳብህ በመቀየር የይግባኝ ጽሁፍህ ለመሳብ ብትፈልግ፡ ለስደተኞች ጽ/ቤት የውድቅ ማድረጉ ውሳኔ እንደ ተቀበልከው ንገራቸው። ፍርድ-ቤቱም የይግባኙ ሂደት ያቆመዋል፡ እንደገናም ኣያየውም

ወደ ኣገርህ መመለስ

የመባረር ውሳኔ በተግባር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ፡ በራስህ ፍላጎት ካገሪቱ ለመውጣት ግዜ ሊሰጥህ ይችላል። በውሳኔው ላይ ካገሪቱ ለመውጣት ስንት ግዜ እንዳለህ ተጽፍዋል። ካገሪቱ በግዜ ለመውጣት ያንተው ሃላፊነት ነው። ወደ ኣገርህ ወይም ልትኖርባት መብት ያለህ ኣገር ለመመለስ ከስደተኞች ጽ/ቤት እርዳታ ታገኛለህ። ለምሳሌ፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ከኣገርህ ጋር ግንኙነት ለመመስረት ወይም የጉዞ ምዝገባ ለማድረግ ሊተባበርህ ይችላል።

ላንዳንድ ሰዎች ወደ ኣገራቸው ተመልሰው በሚያደርጉት የኣዲስ ህይወት ጅማሬ በሚመለከት የኤኮኖሚ እርዳታ ይሰጣቸዋል። ኣንዳንዱም ህግን ወይ ስራ ለማግኘት በሚመለከት ረገድ እገዛ ያገኛሉ። ስለዚሁ ጉዳይ በተጨማሪ ለማወቅ ብትፈልግ ማመልከቻህን ከያዘው ሰው የመልሶ ማቋቋም እርዳታ (återetableringsstödet) በሚመለከት ጉዳይ ጠይቀው።

ስለ ተመልሶ መምጣት የሚመለከት እገዳ

በውሳኔው ላይ በተጠቀሰው ዕለት ካገሪቱ ሳትወጣ ብትቀር፡ የተመልሶ መግባት እገዳ (återreseförbud) ሊበየንብህ ነው። ይህ ማለት፡ ለኣንድ ዓመት ያህል ወደ ሸንገን ኣገሮች፡ እንዲሁም ወደ ቡልጋርያ ወይ ሩመንያ መግባት ኣትችልም ማለት ነው። ስለዚህ ራስህ ከዚህ ሃገር የምትወጣበት ዕለት ኣስታውሰው።

በፍላጎትህ ካገሪቱ ሳትወጣ ብትቀርም በስደተኞች ጽ/ቤት የተመልሶ መግባት እገዳ ሊሰጥህ ነው።

ባስቸኳይ መፈጸም ያለበት የማባረር ደብዳቤ ሲደርስህ፡ የተመልሶ መግባት እገዳም እዛው ኣለ።

ባትተባበር

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ወደ ኣገርህ ለመመለስ የማትተባበር መሆንህን ካረጋገጠ በኋላ፡ የቀኑ ኣበል እንዲቋረጥ ያደርጋል። እንዲሁም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ሊከታተልህና በኣይነ ቁራኛ ሊያይህ እንዲሁም ሊያስርህ ይችላል። መከታተል ማለት ደግሞ በተመደበልህ ግዜና ቦታ ሁሉ ግዜ ሪፖርት ማደረግ ኣለብህ ማለት ነው። በተጨማሪም ፓስፖርትህና የመታወቅያ ሰነዶችህ ለማስረከብ ልትገደድ ነው። በማቆያ ቦታ መሆን ወይ መታሰር ማለት፡ በኣንድ መውጣት የማትችልበት ዝግ ቦታ ትቆያለህ ማለት ነው።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በምታሳየው ኣለመተባበር ምክንያት የማባረር ውሳኔው በተግባር ለማዋል ኣለመቻሉ ሲያረጋግጥ፡ ካገሪቱ ለማባረር ፖሊስ ነው ሓላፊነት የሚወስደው። ፖሊሶች ደግሞ ሊፈልጉህና ኣድነው ሊይዙህ መብት ኣላቸው። ካገሪቱ ለማባረርም ሓይል ሊጠቀሙ ይችላሉ።

ኣዲስ መረጃ ሲገኝ

የውድቅ ማድረግ ውሳኔ ተሰጥቶህ እያለ ተጨማሪ ኣዲስ መረጃ ቢገኝ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ኣዲሱ መረጃው እንዳትባረር የሚረዳህ መሆኑና ኣለመሆኑን ለማወቅ ምርመራ ያካሂዳል። ለምሳሌ፡ ባገርህ ውስጥ ሁኔታው ተባብሶ ሊሆን ይችላል ወይም ኣንተ ራስህ በከባድ በሽታ የተጠቃህ ልትሆን ትችላለህ። ይሁንና፡ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በራሱ ተነሳሽነት ወይም ኣንተ ባቀረብከው ጥያቄ ጉዳዩ ሊመርምረው ይችላል።

ተጨማሪ መረጃ ስትፈልግ

በመጠባበቅ እያለህ የሚጠቅሙህና ኣስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለማወቅ ለበርካታ ግዜያት ስብሰባ ልትጠራ ነው።

በመጠየቅያ ክፍል (ansökningsenheten) የሚገኝ የጉዳይ ኣስኪያጅ/ኣመቻች፡ መኖርያ ቤትንና ኤኮኖሚ እንዲሁም የህጻናት ህክምናና ትምህርት በሚመለከት ምን ዓይነት እርዳታ እንድምታገኝ ሊነግርህ ነው።

የመጠየቅያ ክፍል (ansökningsenheten) የጥገኝነት ማመልከቻህን ከመዘገበው በኋላ፡ በመቀበያው ክፍል ልትመዘገብ ነው። የመቀበያው ክፍል ደግሞ ለቡድን ስብሰባ ሊጠራህ ነው፡ ስለ የምትቀመጥበት ቦታም መረጃ ሊሰጥህ ነው።

ጉዳይህን በሚመለከት ሌላ ኣዲስ ነገር ካለ ለማሳወቅ ዘንድ የመቀበያው ክፍል ለስብሰባ ሊጠራህ ነው። ውሳኔ ከተሰጠህ በኋላ ኣንድ የጉዳይ ኣስኪያጅ/ኣመቻች ስለ ውሳኔው መግለጫ ሊሰጥህ ነው፡ ምን ማድረግ እንዳለብህም ሊነግርህ ነው።

ጥያቄ ቢኖርህ የመቀበያ ክፍሉን ፈልገህ ኣነጋግረው ወይም በሚከተለው የተለፎን ቍጥር 0771-235 235 የደምበኛ ኣገልግሎት ኣነጋግረው። የደምበኛ ኣገልግሎት በሚከተሉት ሰዓታት ብቻ ነው የሚገኝ፤ ሰኞ እስከ ዓርብ 08.00–16.00

በተጨማሪ እዚህ ላይ ኣንብብ www.migrationsverket.se/asylum-amharic.

www.informationsverige.se External link, opens in new window. ስዊድናዊ ሕብረተሰብ ህይወቱ እንዴት እንደሚመራ በተጨማሪ ማንበብ ይቻላል።

ፖሊስ፡ ኣምቡላንስ ወይም እሳት ኣደጋ ለማግኘት 112 ደውል።

ኣስቸኳይ ባልሆኑ ጉዳዮች ከፖሊስ ጋር መነጋገር ከፈለግክ 114 14 ደውል።

ጤናና ህክምና በሚመለከት ኣንዳንድ ጥያቄ ሲኖርህ ወደ 1177 ደውል።

Last updated: