በስዊድን መጠለያና ጥገኝነት ማግኘት

Skydd och asyl i Sverige – amhariska

ለርሶ ስዊድን አገር ጥገኝነት ለጠየቁ የሚያገልግል መረጃ፤ እዚህ ታች ቀርባዋል። በዚህ ጽሁፍ ላይ፤ የጥገኝነት ማመልከቻ ካስገቡና፤ ውሳኔ ከተሰጥዎት በኋላ ምን ሊያጋጥም እንደሚችል መረጃዎች ያነባሉ። እዚሁ ጽሁፍ ላይ በተጨማሪ፤ ጥገኝነት ጠያቂ እንደመሆንዎ መጠንም፤ ስለ ስራ፡ ስለ መኖርያ ቤት፡ ስለ ጤና-ጥበቃና ስለ ገንዘብ እርዳታም በተመለከተ፤ ስላልዎት መብትና ግዴታ ማንበብ ይችላሉ።