የከለላ አሰጣጥ ሕጎች

Asylregler – amhariska

በስዊድን ውስጥ ከለላ እየፈለጉ ከሆነ፣ ወደ ስዊድን በሚገቡበት ጊዜ ለፖሊስ ቦርድ፣ ወይም ለአንዱ የስደተኞች ኤጄንሲ የማመልከቻ ክፍል የከለላ ጥያቄ መመልከቻዎትን ማቅረብ አለብዎ።

የስዊድን የስደተኞች ኤጄንሲ ለስዊድን ኤምባሲ  የቀረበውን  የከለላ ማመልከቻ ማጽደቅ አይችልም።   ስዊድን የመጡት የከላላ ጥያቄ ለማቅረብ ካልሆነ፣ ወደ ዩኤንኤችሲአር/ UNHCR መሄድ ይችላሉ።

የዱብሊን ሕግ ማመልከቻው በየትኛው የአውሮፓ ህብረት አባል አገር  መታየት  እንዳለበት ይወስናል።

ስለዱብሊን ሕግ በይበልጥ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ከለላ ፈላጊዎች

ከለላ ፈላጊ ማለት ወደ ስዊድን የመጣ  እና እዚህ ከለላ ለማግኘት ያመለከተ፤ ነገር ግን ማመልከቻው እስከ አሁን ያልታየ ሰው ማለት ነው።

ለከለላ ፈላጊዎች የመኖሪያ ፈቃድ የሚሰጥባቸው ምክንያቶች

ስዊድን ከስደተኞች ሁኔታ ጋር የተያያዘውን የዩኤን/ UN ስምምነት ፈርማለች። ይህ ማለት፣ ከሌሎች ነገሮች ውስጥ፣ ስዊድን የከለላ ጥያቄዎችን በነፍስ ወከፍ ትመረምራለች ማለት ነው።

የነፍስ ወከፍ ምርመራው  የአመልካቹን የፆታ ሁኔታ እና የግብረስጋ ዝንባሌውን (ይህም ማለት፣ አመልካቹ ግብረ ሰዶማዊ፣ ባለ ሁለት ፆታ ወይም  ጾታውን ያስቀየረ መሆኑ) ግንዛቤ ውስጥ ማስገባትን ያጠቃልላል።

ስዊድን  በዩኤን/ UN ስምምነት መሰረት ስደተኛ ለሆነ ሰው እና፣ እና በአውሮፓ ህብረት/ EU የጋራ ስምምነቶች መሰረት ደግሞ “ድጋፍ እና እርዳታ ለሚሻ ሰው”የመኖሪያ ፈቃድ ትሰጣለች።

ስደተኛ

ስለ ስደተኞች ሁኔታ በሚያትተት የተባበሩት መንግስታት/ UN ስምምነት መሰረት፣ በስዊድን ሕግ እና በአውሮፓ ህብረት EU ሕጎች መሰረት አንድ ሰው ስደተኛ ናቸው የሚባለው ከሚከተሉት ምክንያቶች ውስ ጥ በሆነ መልኩ ስቃይ ይደርስብኛል የሚል ምክንያታዊ ፍርሃት ያላቸው ከሆነ ነው፦

 • ዘር፣
 • የትውልድ አገር፣
 • የሃይማኖት ወይም የፖለቲካ አቋም፣
 • ስነ ጾታ፣
 • የግብረስጋ ዝንባሌ፣ ወይም
 • ከተወሰኑ ማኅበራዊ ቡድኖች ጋር በሚኖር ትስስር

መከራው ከግለሰቡ የትውልድ አገር ባለሥልጣኖች የሚነሳ ሊሆን ይችላል። ባለሥልጣትናቱም ከግለሰቦች ወይም ከቡድኖች ከሚመጣው መከራ ጥበቃ ማድረግ ላይችሉ ወይም ፈቃደኝነት ላይኖራቸው ይችላል።

ፖለቲካ ጥገኛ መሆኑ የታመነለት ሰው፥ በተመድ የስደተኛ ጉባዔና በአውሮፓ ኅብረት ደንብ መሠረት በዓለም ዓቀፍ የታወቀ የፖለቲካ ጥገኝነት ደረጃ የሚከበርለትን ፈቃድ ያገኛል።

የፖለቲካ ጥገኛ መሆኑ የታመነለት ሰው፥ መደበኛው የሶስት ዓመት የመኖሪያ ፈቃድ ይሰጠዋል።

ድጋፍ እና እርዳታ የሚፈልግ ሰው

ድጋፍ እና እርዳታ ያስፈልገዋል ተብሎ የሚታመን ሰው የሚከተሉትን የሚያሟላ ነው፦

 • የሞት ፍርድ ስጋት ያለበት፤
 • የአካላዊ ቅጣት፣ ስቃይ ወይም ሌላ ኢሰብአዊ የሆነ ወይም ሰባዊ ክብር የሚነካ እንግልት ወይም ቅጣት እንደሚደርስበት ስጋት ያለበት፤ ወይም 
 • እንደ ሲቪል ነዋሪ፣ በጦር መሳሪያ ግጭት የተነሳ የአካል ጉዳት ስጋት ውስጥ የሆነ

አማራጭ ጥገኝነት የሚሻ ተብሎ የታመነበት ሰው በአውሮፓ ኅብረት ደንብ መሠረት የአማራጭ ጥገኛነት ፈቃድ ይሰጠዋል።

አማራጭ የከለላ ደረጃ መግለጫ ያለው ሰው እንደ ደንቡ ለ13 ወራት የመኖሪያ ፈቃድ ያገኛል።

ከለላ የማግኘትን መብት የሚከለክሉ ሁኔታዎች

ጉዳይዎ አየታየ ባለበት ጊዜ ውስጥ፥ የጦር ወንጀል፥ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ ወንጀል፥ሌላ ከባድ ወንጀል ፈጽመው የነበሩ መሆንዎን ከደረስንበት ወይም ለሐገሪቱ ደኅንነት ስጋት የሚሆኑ ከሆነ፥ ስዊድን ውስጥ ጥገኝነት ማግኘት አይችሉም። ሆኖም ወደ ትውልድ ሐገርዎ ቢመለሱ የሞት ቅጣት ወይም ሌላ መከራ ሊደርስብዎት የሚችል ከሆነ የጊዜ ገደብ ያለው የመኖሪያ ፈቃድ ሊሰጥዎት ይችላል።

የመኖሪያ ፈቃድ በሌሎች ምክንያት

አንድ ግለ ሰብ የመሳድደ ከለላ ሳያገኝ ወይም ሳታገኝ እንዲሁም ሌላ የመኖሪያ ፈቃድ የሚያስጥ መስፈርትን ሳያሟላ/ሳታሟላ፥ እንዲሁ ልዩ በሆነ ምክንያት ብቻ የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ይችላል/ትችላለች። ይህ እንዲሆን የተለየ አስጨናቂ ሁኔታ መኖሩ መረጋገጥ ይኖርበታል። የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወስነው፣ ግለ ሰቡ የሚገኝበትን የጤና ሁኔታ፥ ከሰዊድን ጋር የመለማመድ አቅሙንና በትውልድ ሃገሩ ያለውን ሁኔታ አጣቃሎ ከግምት በማስገባት ነው።

የሚያስተማማን ሃገረ ትውልድ

የሚያስተማምኑ ሃገረ ትውልዶች የሚባሉትን አገሮች የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት (Migrationsverket) ሥም ዝርዝራቸውን ይዟል። አንድ አገር የሚያስተማማን ሃገረ ትውልድ ነው ተብሎ መፈረጅ እንዲቻል፥ መሟላት ያለባቸው ብዙ መስፈርቶች አሉ።

በስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት እሳቤ የሚከተሉት አገሮች የሚያስተማምኑ ሃገረ ትውልዶች ናቸው፡- (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ከለላ የሚፈልጉ ልጆች

በስዊድን ሕግ መሠረት፣ የስደተኞች ኤጄንሲ በተለየ ሁኔታ ልጆችን ፍላጎት መቀበል አለበት። ድምጻቸውን ማሰማት የሚችሉ እና የሚፈልጉ ሁሉም  ልጆች ይህን የማድረግ ና የመደመጥ  መብት አላቸው ። ከወላጆቻቸው በተለየ ሁኔታ ጥገኝነት የሚፈልጉበት ሌሎች ምክንያቶች ሊኖራቸው ስለሚችል፣ ጥገኝነት የሚፈልግበት የልጁ ምክንያቶች በግል መታየት አለበት።  ጥገኝነት  የሚፈልግ ልጅ ምክንያቶች በሚመረመሩበት ጊዜ፣ ጉዳዩን የሚያየው ሰው ምርመራውን በተቻለ መጠን የልጁን ዕድሜ፣ ጤና እና ብስለት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት። ምርመራው በሚደረግበት ጊዜ ልጁ ከአዋቂ ሰው ጋር የመሆን መብት አለው። ወላጅ ወይም ሌላ ሕጋዊ አሳዳጊ፣ እንክብካቤ ሰጪ፣ እና/ወይም የሕዝብ አማካሪ ጋር ሊሆን ይችላል።

ጥገኝነት ስለሚፈልጉ ልጆች ስለተቀመጠው ደንብ ተጨማሪ ያንብቡ

ተጨማሪ ያንብቡ

 1. ተባበሩት መንግስታት/ UN የስደተኞች ስምምነት (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.
 2. ዩኤንኤችሲአር/ UNHCR (የተመ/UN የስደተኛ ኤጄንሲ) (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.
 3. ህ/ EU የጥገኝነት መመዘኛ ጠቋሚ (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window. 
 4. ውጪ ዜጋ አዋጅ (በስዊድሽኛ ቋንቋ) External link, opens in new window.
 5. ውጪ ዜጋ ሥነ ሥርዓት (በስዊድሽኛ ቋንቋ) External link, opens in new window.
 6. ዱብሊን ሕግ (ባእንግሊዝኛቋንቋ) External link, opens in new window.

Last updated: