የእንግዳ ፓስፖርት (främ­lings­pass) ለማውጣት ስለማመልከት

Ansök om främlingspass – amhariska

እናንት ፖስፖርት የሌላችሁ እና ፓስፖርት ማውጣት የማትችሉ ሰዎች፥ እንደየ ሁኔታው፡ የእንግዳ ፓስፖርት ከስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ማግኘት የምትችሉበት መንገድ አለ። የስዊድን ሃገር ዜግነት እያለዎት ፓስፖርት ማውጣት ከፈለጉ ከፖሊስ ጽ/ ቤት ዘንድ ሄደው የስዊድን ፓስፖርት እንዲሰጥዎት ማመልከት ይኖርብዎታል።

የእንግዳ ፓስፖርት ለማግኘት መሟላት ያለበት

የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት የሚቻለው፡-

 • ከትውልድ ሃገርዎ መንግስት በመሸሽ፥ ስዊድን ውስጥ የጥገኝነት ጠይቀው የመኖሪያ ፈቃድ በማግኘትዎ ምክንያት፥ የአገርዎን ፓስፖርት ማግኘት የማይችሉ ከሆነ፣ ወይም የአገርዎ ፓስፖርት ስዊድን ውስጥ በአንዳንድ ምክንያቶች ተቀባይነት የሌለው እንደሆነ።

በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያት የእንግዳ ፓስፖርት ማግኘት አይችሉም

 • የስዊድን አገር ዜግነት ወይም የአውሮፓ ህብረት አባል/ኢኢኤስ አገሮች (EU/EES) ዜግነት ካለዎት አይሰጥም።
 • የመኖሪያ ፈቃድዎን ያገኙት ከአገርዎ መንግስት ጋር ባልዎት ችግር ምክንያት ጥገኝነት ስለጠየቁ ሳይሆን፥ በሌላ (ለምሳሌ ክብረ ነክ ችግሮች ስለገጠምዎት፥ የተፈጥሮ አደጋ በመከሰቱ ምክንያት ወይም አጠቃላዩ የሃገርዎ ሁኔታ ለእርስዎ ኑሮ አመቺ ባለመሆኑ) ምክንያት ከሆነ። ፈቃድ ያገኙት በእነዚህ በተጠቀሱት ምክንያቶች ከሆነ ፓስፖርት ማውጣት የትውልድ ሃገርዎን ባለሥልጣናት መጠየቅ ይኖርብዎታል።
 • እንደ ፓስፖርት የሚያገለግል፣ ወደ ሌሎች አገራት መጓዝ የሚያስችል አንዳች የጉዞ ሰነድ ካለዎት፣
 • በትውልድ ሃገርዎ ውስጥ እየኖሩ ከሆነ።

የሰደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ጉዳይዎን የሚያየው ለእርስዎ በተሰጠው ውሳኔ ላይ ያሉትን ምክንያቶች መሰረት በማድረግ ሲሆን፥ እያንዳንዱን ጉዳይ ለየብቻ በተናጠል በመመርመር ነው። ከትውልድ ሃገርዎ ፓስፖርት ማውጣት፥ ከፍተኛ ውጣ ውረድ ያለው መሆኑ ወይም እጅግ አስቸጋሪና ከአቅምዎ ብላይ የሆነ ወጪ የሚጠይቅ መሆኑ፥ በራሱ የእንግዳ ፓስፖርት ለማግኘት በቂ ምክንያት አይደለም።

Ett främlingspass

ኤሌክትሮኒክ አገልግሎት (e-tjänsten) ለመጠቀም የሚያስፈልግዎት

የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ለመጠቀም የሚከተሉት ያስፈልጋሉ፡-

 • ስዊድን ውስጥ ተቀማጭ መሆንና ማንነትዎ በህዝብ መዝገብ ውስጥ የሰፈረ መሆኑ
 • የባንክ መታወቂያ (e-identification) ሲኖርዎት
 • ለማመልከቻው የሚከፈለውን ሂሳብ በባንክ የሂሳብ ካርድ ወይም በመክፈያ ካርድ (kontokort eller betalkort) መክፈል መቻል
 • የስዊድን መታወቂያዎ ካርድ አንድ ኮፒ/ቅጂ
 • ምናልባት ቀደም ብሎ የወጣ የእንግዳ መጓጓዣ ሰነድ (främlingspass) ካለዎት፥ እዚያ ላይ ያለውን ማንነት የሚገልዕ ገጽ እና ማሕተም የተደረገባቸውን ገጻት ሁሉ ቅጅ/ ኮፒ ማድረግ ወይም የእንግዳ መጓጓዣ ሰነድ መጥፋቱን የሚገልጽ የፖሊስ ማመልከቻ ማቅረብ።

ከማመልከቻዎ ጋር የፓስፖርት ቅጅ እንዴት አያይዘው መላክ እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ እዚህ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ለልጅ ”የእንግዳ-መጓጓዣ ሰነድ ለማውጣት፥ ከ18 ዓመት በታች ላሉ ልጆች ”Barn under 18 år” በሚል ርዕስ ስር ያለውን መረጃ ያንብቡ

ማንነትዎን ከዚህ በፊት በሚገባ ያላረጋገጡ ከሆነ፥ የትውልድ ሃገርዎን ፓስፖርት ኮፒ ማያያዝ ይችላሉ። ምንም ዓይነት ፓስፖርት ከሌልዎት ግን ሌላ ማንነትዎን ማረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ኮፒ ወይም ቅጂ ማያያዝ ይችላሉ፣ ለምሳሌ መታወቂያ ወረቀት፥ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም ወታደራዊ ደብተር ሊሆን ይችላል።

ከማመልከቻዎ ጋር አያይዘው እንዲያቀርቡ የጠየቅኖትን ሰነዶች በሙሉ ካልላኩልን፥ ውሳኔ የሚያገኙብት ቀን ሊረዝም የሚችል መሆኑን ያስተውሉ።

በኤሌክትሮኒ አገልግሎት (e-tjänsten) ቀነ ቀጠሮ መያዝ

በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት አማካይነት ማመልከቻዎን ከመላክዎ በፊት የጣት አሻራ እና ፎቶግራፍ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። ቀነ ቀጠሮ የመያዙ ሂደት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቱ (e-tjänsten) አንድ አካል ነው።

በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት አማካይነት የያዙትን ቀነ ቀጠሮ የሚሰርዙበትን ወይም የሚቀይሩበትን መንገድ የሚገልጽ መረጃ፥ በኢሜል በምንልከው፣ ማመልከቻ ማስገባትዎን የሚመሰክር ደረሰኝ ላይ ያገኛሉ።

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች በራሳቸው የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት አይችሉም። በልጆቹ ፈንታ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት የሚችለው፤ የልጁ ህጋዊ አሳዳጊ ወይም ህጋዊ ሞግዚት ይሆናል።

ልጅዎ ሁለት አሳዳጊዎች ወይም ህጋዊ ያሉት ከሆነ እና ማመልከቻውን በኤሌክትሮኒክ መንገድ የሚያስገቡ ከሆነ፥ ”Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass” ቅዕ ቁጥር 246011 ማለትም የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ለሆነ ልጅ ”የእንግዳ-ፓስፖርት” ወይም ”የመጓጓዧ-ፓስፖርት” እንዲያወጣለት ፈቃድ የሚሰጠውን ቅጽ ሞልተው በኤሌክትሮኒክ አገልገሎት መላክ ያስፈልጋል። ቅጹ ላይ ሁለቱም አሳዳጊዎች፡ ምስክሮች ባሉበት በፊርማቸው ማረጋገጥ አለባቸው።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ታዳጊ፥ ፓስፖርት (የእንግዳ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ፓስፖርት) እንዲሰጠው መፍቀድዎ የሚገልጹበት ቅጽ፥ ቁጥር 246011 (በሽወደንኛ) Pdf, 657.8 kB, opens in new window.

የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ታዳጊ፥ ፓስፖርት (የእንግዳ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ፓስፖርት) እንዲሰጠው መፍቀድዎ የሚገልጹበት ቅጽ፥ ቁጥር 247011 (በእንግሊዝኛ) Pdf, 701.3 kB, opens in new window.

ማመልከቻውን የሚያስገቡት እንደ ሞግዚት በመሆን ከሆነ፥ የሞግዚትነት ሥልጣን ማስረጃ ሰነድ እና መታወቂያ ወረቀትዎን አያይዘው መላክ ይኖርብዎታል።

ወላጆቹ ስዊድን ውስጥ የሌሉ ልጅ ፎቶግራፍ ለመነሳትም ሆነ የጣት አሻራ ለመስጠት በሚሄድበት ግዜ፥ የልጁ ህጋዊ ሞግዚት አብሮት መሄድ ይገባዋል።

የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከቻ ከሚያስገቡ ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ የተወሰነ ክፍያ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ። ክፍያውን ማመልከቻውን ሲያስገቡ ሲሄዱ በካርድ ይከፍላሉ።

ክፍያውን በካርድ መክፈል የማይችሉ ከሆነ በባንክጊሮ (bankgiro) በኩል መክፈል ይችላሉ። አልያም የጣት አሻራ ለመስጠት እና ፎቶግራፍ ለመነሳት ሲሄዱ፥ የመክፈያ ወረቀት እንዲሰጥዎት የሚያስተናግድዎትን ሰው ይጠይቁና፥ ሌላ ግዜ ወረቀቱን በመጠቀም መክፈል ይችላሉ።የተጠቀሰው ክፍያ ገቢ እስኪሆን ድረስ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ማመልከቻውን መመልከት አይጀምርም።

ለእንግዳ ፓስፖርት የሚደረጉ ክፍያዎች (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት በኢንተርኔት (webben) ማመልከቻ ማስገባት የማይችሉ ከሆነ “Ansökan om främlingspass" የሚባለው ቅፅ፥ ቁጥር 190011” መሙላትና፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት የፈቃድ ልዩ ክፍል ድረስ በአካል ሄድው ማስገባት ይችላሉ። ወደ ጽ/ ቤት ከመምጣትዎ በፊት ቅጹ መሞላት አለበት።

ለእንግዳ ፓስፖርት ለማመልከት፡ ቅፅ ቁጥር 190011 ይጠቀማሉ (በስዊድንኛ) Pdf, 732.6 kB, opens in new window.

ለእንግዳ ፓስፖርት ለማመልከት፡ ቅፅ ቁጥር 191011 ይጠቀማሉ (በእንግሊዝኛ) Pdf, 1.2 MB, opens in new window.

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች

ከ18 ዓመት በታች ያሉ ልጆች በራሳቸው የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት አይችሉም። በልጆቹ ፈንታ የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ማመልከቻ ማስገባት የሚችለው፥ የልጁ ህጋዊ አሳዳጊ ወይም በህግ ሥልጣን የተሰጠው ሞግዚት ነው።

የልጁ አሳዳጊዎች እንደ መሆዎ መጠን፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከ18 ዓመት ዕድሜ በታች ለሆነ ልጅ (የእንግዳ-ፓስፖርት” ወይም ”የመጓጓዧ-ፓስፖርት) ሰነድ እንዲያወጣለት ፈቃድ የሚሰጠውን ቅጽ ”Medgivande att Migrationsverket får utfärda pass” ቁጥር 246011 ሞልታችሁ ከማመልከቻው ጋር ማስገባት አለባችሁ። አሳዳጊዎች ሁለት ከሆኑ ሁለቱም መፍቀዳቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ታዳጊ፥ ፓስፖርት (የእንግዳ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ፓስፖርት) እንዲሰጠው መፍቀድዎ የሚገልጹበት ቅጽ፥ ቁጥር 246011 (በሽወደንኛ) Pdf, 657.8 kB, opens in new window.

የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆነው ታዳጊ፥ ፓስፖርት (የእንግዳ ፓስፖርት ወይም የጉዞ ፓስፖርት) እንዲሰጠው መፍቀድዎ የሚገልጹበት ቅጽ፥ ቁጥር 247011 (በእንግሊዝኛ) Pdf, 701.3 kB, opens in new window.

ወላጆቹ ስዊድን ውስጥ የሌሉ ልጅ፥ ፎቶግራፍ ለመነሳትም ሆነ የጣት አሻራ ለመተው በሚሄድበት ግዜ፥ የልጁ ህጋዊ ሞግዚት አብሮት መሄድ ይገቧል። በተጨማሪ፡ የልጁ ህጋዊ ሞግዚት፥ የሞግዚትነት ሥልጣን ማስረጃ ሰነድ እና መታወቂያ ወረቀቱን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

ቀነ-ቀጠሮ ይያዙ

ማመልከቻዎን ለማስገባት ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ከመሄድዎ በፊት፥ ቀነ- ቀጠሮ መያዝ ያስፈልጋል። የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ለሚፈልግ እያንዳንዱ ግለ-ሰብ፥ የየራሱን ቀጠሮ መያዝ እንዳለበት ሁሉ፥ እያንዳንዱ ግለ-ሰብ የየራሱን ማመልከቻ በተናጠል ማስገባትም ይኖርበታል።

ማመልከቻዎን ለማስገባት ቀነ-ቀጠሮ ይያዙ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ማመልከቻዎን ሲያስገቡ

ማመልከቻዎን በሚያስገቡበት ግዜ፥ መያዝ የሚገባዎት ሰነዶች

 • የስዊድን አገር መታወቂያ
 • የማመልከቻ ፎርም ወይም ቅጽ፥ የተሞላና የተፈረመበት (እያንዳንዱ አመልካች የየራሱ አንዳንድ ፎርም ወይም ቅጽ)
 • የእንግዳ ፓስፖርት ቀድሞ ተሰጥቶት ከነበረ፥ የእሱን አንድ ኮፒ ወይም ጠፍቶብዎት ከሆነ፥ ፓስፖርቱ መጥፋቱን የሚያሳይ ለፖሊስ ያስገቡት ማመልከቻ አንድ ኮፒ ወይም ቅጂ።
 • የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት፡ ከ18 ዓመት በታች ለሆነ ታዳጊ ፓስፖርት (የእንግዳ ፓስፖርት ወይም የመጓጓዣ ፓስፖርት) እንዲሰጠው የመፍቀዳቸው ቅፅ፥ ቁጥር 246011ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ማንነትዎን ከዚህ በፊት በደንብ ያላረጋገጡ ከሆነ፥ የትውልድ ሃገርዎን ፓስፖርት አንድ ኮፒ ማያያዝ ይችላሉ። ምንም ዓይነት ፓስፖርት ከሌልዎት ግን፥ ሌላ ማንነትዎን ማረጋገጥ የሚያስችል ሰነድ ኮፒ ማያያዝ ይችላሉ፣ ለምሳሌ መታወቂያ ወረቀት፥ የልደት ምስክር ወረቀት ወይም ወታደራዊ ደብተር ሊሆን ይችላል።

የትውልድ ሃገርዎ ፓስፖርት ወይም የተቃጠለ የእንግዳ ፓስፖርት (främlingspass) ካለዎት፥ እነዚህን ፓስፖርቶች ለስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት መመለስ አለብዎት። አንዳንድ ግዜ ጉዳይዎን የሚያስተናግደው ጸሃፊ (handläggaren) የፓስፖርት ኮፒ ብቻ ትተው እንዲሄዱ ሊነግርዎት ይችላል፣ ይሁን እንጂ ጉዳይዎ ውሳኔ ሊሰጥበት መታየት ሲጀምር ወይም ውሳኔ ተሰጥቶበት አዲሱን ፓስፖርት ሊወስዱ ሲመጡ፥ ኦሪጅናሉን ፓስፖርት እንድያስረክቡ መጠየቅዎ አይቀርም።

ማመልከቻዎን ሊያስገቡ ሲመጡ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ፎቶግራፍ ያነሳዎታል፥ የእጅ አሻራዎንም ይወስዳል። ፎቶዎ፥ የእጅ አሻራውና ሌላው እርስዎን የሚገልጽ መረጃ ሁሉ፥ በአንድ ዳታ-ቺፕ ውስጥ ተጠናቅሮ የእንግዳ ፓስፖርትዎ ላይ ይቀመጣል። እነዚህ መረጃዎች የስደተኞች ጉዳይ ጽ /ቤት ጋር ከቶ አይቀመጡም። መረጃዎቹ የሚገኙት የእንግዳ ፓስፖርትዎ ላይ ካለው ዳታ-ቺፕ ውስጥ ብቻ ነው። ከስድስት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች፥ የጣት አሻራ መስጠት አይጠበቅባቸውም።

የእንግዳ ፓስፖርት ለማውጣት ከሚያመለክቱ ስዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ክፍያ ይጠየቃሉ። ክፍያውን ማመልከቻ ለማስገባት ወደ ፈቃድ ዋና ክፍል ሲሄዱ በካርድዎ መክፈል ይችላሉ። ሌላው አማራጭ፥ የመክፈያ ወረቀት በመውሰድ ክፍያውን ሌላ ግዜ ማከናዎን ይቻላል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ግን የተጠቀሰው ክፍያ ገቢ እስኪሆን ድረስ ማመልከቻውን መመልከት አይጀምርም።

ለእንግዳ ፓስፖርት የሚደረጉ ክፍያዎች (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ደረ-ገጽ ላይ የእርስዎን ጉዳይ ውሳኔ እስዲያገኝ በአሁኑ ወቅት ባለው የሥራ ሁኔታን ከግምት በማስገባት ምን ያህል ግዜ ሊያስጠብቅዎት እንደሚችል ማየት ይችላሉ። በጉዳይዎ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች እንዲያቀርቡ የሚጠየቁበት አጋጣሚ ከተከሰተ፣ ውሳኔ ለማግኘት ከሚጠበቀው በላይ ረዘም ያለ ግዜ ሊወስድብዎት ይችላል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የእርሶ ጉዳይን ተመልክቶ ሥራውን ሲያጠናቅቅ፥ ውሳኔውን በፖስታ ወደ እርስዎ ይልካል።

ባሁኑ ወቅት ማመልከቻዎች ለመወሰን የሚወስደው ጊዜ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ውሳኔው በፖስታ እቤትዎ ድረስ ይላካል። የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የእንግዳ ፓስፖርት የማግኘት መብት እንዳልዎት ከወሰነልዎት፥ ፓስፖርቱ ተሰርቶ ካለቀ በኋላ መጥተው እንዲወስዱ የሚያሳስብ መልዕክት እንዲደርስዎት ያደርጋል። ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ፓስፖርት ለማግኘት ማመልከቻ ካስገቡበት የፍቃድ ዋና ክፍል ድረስ መጥተው እስኪወስዱ እስከ 14 ቀናት ግዜ ሊያስጠብቅ ይችላል።

ማመልከቻዎ ውድቅ ከሆነስ

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የእንግዳ ፓስፖርት ማመልከቻዎን ውድቅ እንዲሆን ከወሰነ፥ ውሳኔውን ይግባኝ ማለት የሚችሉት፣

ይግባኝ የሚሉ ከሆነ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የትኛውን ውሳኔ እንዲለውጥሎት እንደፈለጉ፥ ውሳኔው ምን ላይ ስህተት እንዳለበት በሚገልጽ መልኩ፥ ደብዳቤ ጽፈው ማስገባት አለብዎት። ደብዳቤው ላይ የእርስዎን ማንነት የሚገልጹ መረጃዎች፥ የጉዳዩ መዝገብ ቁጥር እና የእርስዎ የራስዎ ፊርማ በሚገባ መስፈር ይኖርበታል።

የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ውሳኔ በሰጥዎት በሶስት ሳምንት ግዜ ውስጥ፥ የይግባኝ ጥያቄዎን ማስገባት እንዳለብዎት ልብ ይበሉ።

ይግባኙን በእርስዎ ፈንታ ሌላ ሰው እንዲያደርግልዎት ከፈለኩ፥ ለግለ-ሰቡ የውክልና ሥልጣን በጽሑፍ መስጠት ይኖርብዎታል።

የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት የተፈቀደላችሁ ሰዎች፥ ፓስፖርታችሁን ለመውሰድ ወደ ስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ከመምጣታችሁ በፊት፥ ቀነ-ቀጠሮ መያዝ ይኖርባችኋል። ለያንዳንዱ ፓስፖርት ወሳጅ የየራሱን ቀነ-ቀጠሮ መያዝ እንዳለባችሁ መገንዘብ ያስፈልጋል። የልጆችዎን ፓስፖርት ለመውሰድ ወደ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የሚመጡ ከሆነ፥ ቀደም ብለው ለእያንዳንዱ ልጅ ፓስፖርት ቀነ-ቀጠሮ መያዝ ይገባል።

የእንግዳ ፓስፖርትዎን ከሌላ ቦታ ሄደው እንዲወስዱ የሚገልጽ አንዳች መልዕክት ካልደረሰዎት በቀር፥ ፓስፖርቱን ማመልከቻ ካስገቡበት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ፍቃድ ክፍል (tillståndsenhet) ወይም አገልግሎት መስጫ ጣቢያ (servicecenter) ድረስ ሄደው ይወስዳሉ። የእንግዳ ፓስፖርት እንዲያወጡ በሚፈልጉበት ግዜ፥ እርሶ በሚፈልጉት ልዩ ቦታ ሄደው ማምጣት የሚፈልጉ ከሆነ፥ ይህንኑ ፍላጎትዎን ፎቶግራፍ ሲነሱና የእጅ አሻራ ሲስጡ ለሚያገኙት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት ጸሐፊ ያሳውቁ።

ፓስፖርትዎን ራስዎ በአካል ሄደው ነው ማውጣት የሚችሉት። ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች አሳዳጊታቸው ወይም የሞግዚትነት ሥልጣን የተሰጠው ሰው (gode mannen)፥ ከፈለገ ልጆቹን ሳያስከትል፥ መጥቶ መውሰድ ይችላል።

ከ15 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች ራሳቸው በአካል መጥተው መውሰድ የሚችሉት፤ አሳዳጊያቸው ቀደም ብሎ ማመልከቻ ባስገባበት ወቅት፥ ልጁ ራሱ ብቻውን መጥቶ እንደሚወስድ አሳውቆ ከነበረ ነው።

የእንግዳ ፓስፖርትዎን ለመውሰድ ሲመጡ፥ አንድ የጸና ማለትም የአገልግሎት ግዜው ያልወደቀ መታወቂያ ይዘው እንዲመጡ ያስፈልጋል። በፊት ያወጡትን የእንግዳ ፓስፖርት ቀደም ብለው ያላስረከቡ ከሆነ፥ አሁን አዲሱን ለመውሰድ ሲመጡ ማስረክብ ይኖርቦታል።

የእንግዳ ፓስፖርት መጥተው ለመውሰድ ቀነ-ቀጠሮ ይያዙ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

በእንግዳ ፓስፕርት መጓዝ

የእንግዳ ፓስፖርት የአውሮፓ ህብረት የመጓጓዣ ሰነዶች መስፈርቶች የሚያሟላ ሰነድ ስለሆነ ወደ ሁሉም አገሮች ሊጓዙበት ይችላሉ። ወደ አንዳንድ አገሮች ሲጓዙ የአገሮቹ ቪዛ ሊያስፈልጎት ይችላል። ስለዚህ ወደ እነዚህ አገሮች ከመጓዝዎ በፊት የበለጠ መረጃ ለማግኘት የሃገራቱን ቆንስላዎች ያነጋግሩ።

እርስዎ ፈቃድ ያገኙት በጥገኝነት ጥያቅ ምክንያት ከሆነ፥ በእንግዳ ፓስፕርት ላይ ወደ ትውልድ ሃገርዎ ወይም እንዲሰደዱ ያስገደድዎት ሃገር ዘንድ መጓዝ የማይችሉ መሆንዎን የሚገልጽ ምልከታ በእንግዳ ፓስፖርትዎ ላይ ይሰፍራል።

ማንነትዎን በደንብ ሊያረጋግጡ ያልቻሉ ሰው ከሆኑ፥ በእንግዳ ፓስፖርትዎ ላይ ማንነትዎ በደንብ ያልተረጋገጠ ሰው እንደሆኑ የሚገልጽ ምልከታ ይሰፍራል፣ ይህ ምልከታ ወደ አንዳድ አገሮች የሚያደርጉትን ጉዞ አስቸጋሪ ሊያደርግብዎት ይችላል።

ፓስፖርቱ የሚጸናበት ግዜ

የእንግዳ ፓስፖርት (Ett främlingspass) ጸንቶ የሚቆየው ቢረዝም እስከ ሶስት ዓመት ነው። የእንግዳ ፓስፖርትን ማራዘም አይቻልም። ጸንቶ የሚቆይበት ግዜ በማለቁ ምክንያት አዲስ የእንግዳ ፓስፖርት ማውጣት ካስፈለግዎት ግን እንደገና አዲስ ማመልከቻ ማስገባት ይኖርብዎታል።

አዲስ የእንግዳ ፓስፖርት ሲያወጡ፥ አሁንም እንደገና ፎቶግራፍ መነሳትና የጣት አሻራ እንዲሰጡ ይጠየቃሉ። በፊት የሰጡት ፎቶግራፍና የጣት አሻራ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት የመረጃ ቋት ወይም ዳታ ቋት ውስጥ አይቀመጥም።

ፓስፖርቱ ከጠፋብዎትስ

የእንግዳው ፓስፖርት ከጠፋብዎት ወይም ከተሰረቀ፥ በመጀመሪያ ለፖሊስ ማመልከት ይኖርብዎታል። በጠፋው ምትክ አዲስ ማውጣት የሚፈልጉ ከሆነ፥ አዲስ ማመልከቻ ማስገባት የግድ ነው። ፖሊስ በመኖሪያ ድራሻዎ የሚልከውን የማመልከቻዎን ቅጂ ወይም ኮፒ ወይም መጥፋቱን በሚያመለክቱበት ግዜ፥ እዚያው በእጅዎ የሚሰጥዎትን የማመለከቻዎን ቅጂ ወይም ኮፒ ይዘው ይምጡ።

ፓስፖርት ሲጠፋ የጉዞ መዳረሻን ስለመገደብ

የእንግዳ ፓስፖርትዎ ከጠፋብዎት ወይም ፓስፖርቱ ያለአግባብ ጥቅም ላይ ሳይውል አይቀርም የሚል ጥርጣሬ ካለ፥ የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ ቤት አዲሱ የእንግዳ ፓስፖርት ላይ የጉዞ መዳረሻው ገደብ ሊጥልበት ይችላል። ይህ ማለት፡ አዲሱ የእንግዳ ፓስፖርትዎ መጓዝ የሚያስችለው ስዊድን፣ ዴንማርክ፡ ፊንላንድ፡ አይስላንድና ኖርወይ ውስጥ ብቻ ይሆናል። ከአንድ በላይ የእንግዳ ፓስፖርት ጠፍቶብዎት ከሆነ፣ መዘዙ አዲሱ ፓስፖርትዎ ላይ ስዊድን ውስጥ ብቻ መጓዝ የሚያስችል የመዳረሻ ገደብ እንዲጣልበት የሚያደርግ ይሆናል።

የእንግዳ ፓስፖርትዎ የተሰጠዎት እንደ አማራጭ ጥገኝነት የሚያስፈልገው ሰው (alternativt skyddsbehövande) ከሆነ ግን፥ ይህ የጉዞ መዳረሻን የመገደብ ደንብ እርስዎን የሚመለከት አይሆንም።

Last updated: