ስዊድን ውስጥ ከሚኖር ሰው ልጅ ወይም ጽንስ ካለዎት

Om du har eller väntar barn i Sverige – amhariska

የስዊድን ዜጋ የሆነ ወይም በስዊድን ውስጥ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ልጅ ካለዎት በተወሰኑ ሁኔታዎች ከልጁ ጋር ባለዎት ግንኙነት ምክንያት፣ ከስዊድን መውጣትን ሳያስፈልግዎት  የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ።

በተለምዶ በስዊድን ውስጥ ከቤተሰብ አባል ጋር አብሮ መኖር የሚፈልግ ሰው በስዊድን ኤምባሲ በኩል ለመኖሪያ ፈቃድ ማመልከት አለበት ወይም በእርሱ ወይም በእርሷ የትውልድ አገር፣ ወይም በሌላ የመኖሪያ ፈቃድ ባለው ወይም ባላት አገር ውስጥ አጠቃላይ ምክር ማግኘት አለበት። የመኖሪያ ፈቃድ አንድ ሰው ወደ ስዊድን ከመጓዙ በፊት ሊሰጠው ይገባል።

በስዊድን ውስጥ ነዋሪ ከሆነ ስው ጋር ባለ ቤተሰባዊ ትሥር ምክንያት የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት ምን እንደሚያስፈልግ በይበልጥ ያንብቡ። (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ስዊድንን ለቀው ሳይወጡ የፈቃድ ጥያቄ ስለማቅረብ

ለጥገኝነት ካመለከቱ እና  በስዊድን ከሚኖር ሰው ልጅ ወይም ጽንስ ካለዎ  በተወሰኑ ሁኔታዎች ስዊድንን መልቀቅ ያሳይስፈልግዎ የመኖሪያ ፈቃድ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው በስዊድን የመኖር ፈቃድ ያለው ወይም የስዊድን ዜግነት ያለው ልጅ ካለዎት፣ ወይም ከስዊድናዊ ዜጋ ወይም በቋሚነት የመኖሪይ ፈቃድ ካለው ሰው ጽንስ ካለዎት ነው።

ከልጅዎት ጋር ላለመለየት ብለው በስዊድን ለመኖር ከፈለጉ፣ ስለቤተሰብዎ ሁኔታ ለስደተኞች ኤጄንሲ መናገር አለበዎት። ስለ ልጅዎት ወይም ስላልተወለደ ልጅዎ ሁኔታ ለመግለጽ ደብዳቤ ይጻፉ። ወደ ትውልድ አገርዎ በመጓዝ ከዚያ ሆነው ለመኖሪያ ፈቃድ ለማመልከት፣ ለምን ከልጅዎ   እንደማይችሉ ይግለፁ፤  እንዲሁም ዝምድናዎን ወይም እርግዝናዎን የሚያሳይ ሰርቴፊኬቶች አካተው ይግለጹ። በተጨማሪም  ‘በስዊድን ለመኖር የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ፣ የቅጹ ቁጥር 160011’ የሚለውን ቅጽ ይሙሉ እና ያካቱ።

በስዊድን ለመኖር የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ፣ ቅጽ ቁጥር 160011 (በስዊድሽኛ ቋንቋ) Pdf, 818.7 kB, opens in new window.

በስዊድን ለመኖር የመኖሪያ ፈቃድ ማመልከቻ፣ ቅጽ ቁጥር 161011 (ባእንግሊዝኛቋንቋ) Pdf, 869.6 kB, opens in new window.

ለስደተኞች ኤጄንሲ በማንኛውም ሰዓት በስዊድን በሚገኙ ጊዜ፣ ልጅዎ ቢወለድም ወይም ማመልከቻዎትን ለስደተኞች ኤጄንሲ ወይም ለስደተኞች ፍርድ ቤት ያስረከቡ ቢሆንም የቤተሰብዎን ሁኔታ መግለጽ ይችላሉ።

ወደ አገር ለመግባት የሚከለክል ውሳኔ ከተቀበሉ ወይም ከአሁን በኃላ አቤቱታ ለማቅረብ የሚይችሉበት እና ወደ አገርዎ የሚላኩ ከሆነ፣ ነገር ግን ከልጅዎት ጋር ካልዎት ግንኙነት የተነሳ በስዊድን ለመቆየት ከፍለጉ ምን ማድረግ እንዳለብዎት የበለጠ ያንብቡ።

Last updated: