የጥገኝነት ጥያቄዎ ተቀባይነት ሳያገኝ ሲቀር

Om du får avslag på din ansökan – amhariska

ጥያቄዎ ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረ እንደሆን፥ “ሚግራሾስንቨርከት” ስዊድን አገር ውስጥ ለመቆየት በቂ ምክንያት የለዎትም ብሎ ስላመነበት ነው። ተቀባይነት ባያገኙ ሁለት ምርጫዎች አለዎት፡- ውሳኔውን ተቀብለው ወደ ትውልድ አገርዎ መመለስ ወይም ውሳኔውን ይገባኝ ማለት ነው። ይግባኝ ለማለት ከመረጡ፥ ፍርድ ቤቱ ውሳኔዉ እንደገና ይመለከቷል። ይግባኝ ለማለት ቢመርጡም፥ የመመለስዎን ዕቅድ ማድረግ ይኖርብዎታል።

ካገር የመልቀቅ ወይ የመባረር ውሳኔውን እሺ ብለው ከተቀበሉት፥ “በደስታ-የመቀበል እወጃ” (nöjdförklaring) የተባለውን ሰነድ ይፈርማሉ። “በደስታ-የመቀበል እወጃ” (nöjdförklaring) ሰነድ አንዴ ከፈረሙበት፥ እንደገና ይግባኝ ማለት ኣይችሉም፥ ስለዚህ ወደ አገርዎ የመመለስ ዕቅድ ማስተካከል ይገቧታል። “በደስታ-የመቀበል እወጃ” (nöjdförklaring) ሰነድ ባይፈርሙበትም እንኳን፥ ወደ አገርዎ ስለመመለስዎ ጉዳይ፥ “ከሚግራሾንስቨርከት” ጋር ተባብረው መስራት አስፈላጊ ነው።

ውሳኔው ለአራት ዓመታት የጸና ይሆናል።

የእርሶ ከስዊድን አገር ስለመልቀቅ የሚመለከት ደንብ ተጨማሪ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ለመመለስ የሚደረግ ድጋፍ

እንደ መጡበት አገር ታይቶ፡ በአገርዎ የሚኖሩት የመጀሚሪያው ጊዜዎን እንዲቀልልዎት ለማደርግ፥ የገንዘብ ድጋፍ ወይም ሌላ የድጋፍ እርምጃዎች የማግኘት ዕድል ይኖርዎታል።

ሲመለሱ ይህን ድጋፍ ማግኘት የሚችሉ እነማን እንደሆኑ የበለጠ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ውሳኔው ሳያከብሩ ቢቀሩ

በውሳኔው ሰነድ ላይ በተሰጥዎ የጊዜ ገደብ ውስጥ፥ ስዊድን አገር ለቀው ባይወጡ፥ ”ከሚግራሾንስቨርከት” የሚሰጥዎ የመጠለያ ቤትና የገንዘብ እርዳታ የማግኘት መብትዎ ያቆሟል። መልሶ ወደ አገሪትዋ የመግባት እገዳም እንዲጣልብዎ ያደርጋል።

”ሚግራሾንስቨርከትም” አገር ለቀው እንዲወጡ እስከሚደረግ ድረስ፥ በቁጥጥር ሥር ሊያውልዎት ወይም በእስር ቤት እንዲቆዩ ሊወስን ይችላል። “ሚግራሾንስቨርከት” የርሶ አገር ለቀው የማውጣት ኃላፊነቱም ወደ ፖሊስ ለማስተላለፍ ይችላል።

በቁጥጥር ስለ ሟልና ስለ እስር ቤት የበለጠ ያንብቡ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ይግባኝ ማለት

”የሚግራሾንስቨርከት” ውሳኔ ካልተቀበሉት፥ ይግባኝ ለማለት (አቤቱታ ማቅረብ) መብት አልዎት። ወደ ”ሚግራሾንስቨርከት ፍርድቤት” አቤቱታ በሚያቀርቡበት ጊዜ፥ ”የሚግራሾንስቨርከት” ውሳኔ እንደገና እንዲታይልዎት ጥያቄ አቅርቧል ማለት ነው። የይግባኝ ጥያቄ፥ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ማቅረብ ይኖርብዎታል። የተሰጥዎት ጊዜ፡ ውሳኔ በተጻፈበት ግልባጭ ላይ ሰፍሮ ያገኙታል።

ይግባኝ እንዴት መጠየቅ እንደሚችሉና ምን ያህል ጊዜ እንደተስጥዎት የበለጠ ያንብቡ

ጉዳይዎ የመጣል ውሳኔ ከተሰጠው በኋላ የሚፈጠር አዲስ ክስተት

መመለስ የማይችሉበት ክስተት (ሁኔታ) ከተፈጠረ፥ ይህንኑ ለተቀበልዎት ያስተዳደር አካል (mottagningsenhet) ሁኔታውን ያሳውቃሉ። ”ሚግራሾንስቨርከት” ይህንን ይመለከት እና፥ ከአገር የማባረር ውሳኔውን ለማካሄድ የሚያስቸግር ሁኔታ ካለ ያጣራል። ይህንኑ የሁኔታው መረጃ፥ ውሳኔ ከተሰጦ በኋላ የተከሰተ አዲስ ሁኔታ መሆን ይኖርበታል።

ጉዳይዎ የመጣል ውሳኔ ከተሰጠበት በኋላ፥ ተቀባይነት ስላለው መረጃ የበለጠ ያንብቡ

Last updated: