ኣንተ መሆንክን ማረጋገጥ ኣለብህ

Berätta vem du är – amhariska

የስደተኞች መጠለያ ጽሕፈት ቤት የስደተኝነት ጥያቄ ለማቅረብ ብትወስን፤ ኣንተ መሆንክንና፤ ከየት ቦታ እንደመጣህ ማረጋገጥ ኣለብህ። ኣንተን መሆንክን የሚያረጋግጡ ኣስፈላጊዎች ነገሮች፤ ተቀባይነት ያላቸው መታወቅያ ወረቀት ማቅረብ ያስፈልጋል።

አንተን መሆንክን ፤ ከየት እንደመጣህ የሚያረጋግጥ ፓስፖርት ወይንም መታወቂያ ወረቀት ከኣገርህ ከመንግስታዊ ጽሕፈት ቤት ያወጣኸው ወረቀት ስዕልህ የተለጠፈበት መሆን ኣለበት። እመታወቂያ ወረቀቱ ደግሞ ስምህና፤ዜግነትህ፤መታወቂያው መቸ እንደተሰጠህ መስፈር ኣለበት። የስደተኝነት ጥያቄ ስትጠይቅ መታወቂያ ወረቀትህ ታቀርባለህ።

ምናልባት ፓስፖርት ወይንም መታቂያ ወረቀት ከሌለህ

ፓስፖርት ወይንም መታወቂያ ወረቀት የስደተኝነት ጥያቄ ስትጠይቅ ከሌለህ፤ መታወቂያ ወረቀት እንድታቀርብ የተወሰነ ጊዜ ቀጠሮ እንሰጥሃለን። ማስረከብ ያለብህን ወረቀቶችና መቸ ማቅረብ እንዳለብህ ቀጠሮ እንሰጥሃለን።

ምናልባት ሌሎች ዓይነቶች መታወቂያዎች ወረቀቶች ቢኖርብህ፤ ለምሳሌ የመኪና መንጃ ፈቃድ፤ የልደት ማረጋገጫ (የተወለድክበት ማረጋገጫ)፤ የዜግነት ማረጋገጫ፤ የወታደርነት መጽሐፍ ልታቀርብ ትችላለህ። እነዚሁ ወረቀቶች እያንዳንዱ መረጋገጫ ሊሆኑ ኣይችሉም፤ ብዙ የተለያዩ ወረቀቶች ተጠቃልለውና በምትሰጠው ቃሎች ተያይዝው፤ ያንተ መሰረትና፤ ስለ ኣገርህ የሰጠኸው መግለጫ ተደምሮ፤ ዜግነትህ ምናልባት ለማረጋገጥ ይቻላል።

ማታወቂያ ወረቀት ለማቅረብ ከተተባበርክን የስደተኝነት ጥያቄህን ውሳኔ እስኪወሰን ድረስ እንድትሰራ ይፈቀድልሃል፤ የግድ የስራ ፈቃድ እንዲኖረብህ ኣለበት ከሚል ሕግ ነጻ ነህ (ኤይቲ-ኡንድ)።

የጥገ ኝነት ጉዳይህን እስኪጣራ ለመስራት (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

ኣንተ መሆንክን የሚያረጋግጥ ማረጋገጫ ለማቅረብ ያንተ ሓላፊነት ነው። ምናልበት መታወቂያ ወረቀት ለማቅረብ የማትችል ከሆንክ፤ ያደረግከውን ጥራትና ድካም ለስደተኞች መጠለያ ጽሕፈት ቤት ትገልጻለህ፤ ምናልባት ጥራትና ድካም ባታደርግ ግን የስደተኞች መጠለያ ጽሕፈት ቤት በየቀኑ የሚሰጥህ የገንዘብ ዕረዳታ ቀንሶ ይሰጥሃል።

ስለ በየቀኑ የሚሰጥ የገንዘብ ዕርዳታ በተጨማሪ ኣንብብ

ኣንተን መሆንክን መታወቂያ ወረቀት ከሌለህ

እስዊድን ኣገር መተወቂያ ወረቀት ካለቀረብክ የጥገኝነት ፈቃድ ሊሰጥ ይቻላል። ደምበኛ ማረጋገጫ፤ ማስታወቂያ ከሰጠህ፤ ማን መሆንክንና ፤ ከየት እንደመጣህ ፤ ከገለጽክ በቂ ሊሆን ይችላል።ፓስፖረት ወይንም መታወቂያ ወረቐት ካገር ቤተ ለማመጣት ካቀጠህ፤ የስዊድን ዜግነት በምትጠይቅበት ጊዜ ኣንተ መሆንክነ የሚል ጉደይ ከበድ ያለ ጭኖት ይደርስብሃል፤ የዜግነት ጊዜ ትያቄህ ረጅም ጊዜ ሊፈጅ ይችላል።

ስለ መተወቂያ ለማረጋገጥ የስዊድን ዜግነት ለመውሰድ ጥያቄ ለማንበብ ትችላለህ (ባእንግሊዝኛቋንቋ)

እውነት ያልተመረኮሱ ነገሮች ስለ ማታወቂያ ካቀረብክ፤ ውሸት መሆኑን ከተጋለጠ ከስደተኞች መጠለያ የተሰጠህ የመኖሪያና የስራ ፈቃድህ ይሰረዛል፤ ስዊድን ኣገር ለቀህ እንድወጣ ውሳኔ ይሰጣል። በ ኢንተርነት ኣድረገህ የዜግነት ወረቀት ትሞላለህ። እታች ያለወን ነው።

Last updated: